Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Friday, November 30, 2012

"የኢትዮጵያ ዘመናዊ የህፃናት የውጭ ንግድ"

የጉዲፈቻ ታሪክ በኢትዮጵያ በባህላዊ መንገድ ሲደረግ የቆየ ነው መቼ እንደተጀመረ በእርግጠኝነት ለማወቅ ባይቻልም በ18 ክፍለ ዘመን በኦሮሞ ብሔረሰብ እንደተጀመረ ይታሰባል። ጉዲፈቻ የሚለው ቃል የመጣው ከኦሮሚኛ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ተፈጥሮዓዊ የወላጅነትና የልጅነት የሥጋ ዝምድና ሳይኖር ከሌላ ሰው አብራክ የተወለደን ልጅ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ጥቅሙን ጠብቆ እንደ አብራክ ክፋይ ልጅ ማሳደግ ማለት ነው በኢትዮጵያ የጉዲፈቻ ሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1952 ዓ.ም. በወጣው የፍታብሔር ሕግ የሕግ ማዕቀፍ ተሰጥቶታል ይህም ሕግ የሕፃኑን መብት የሚያስጠብቅ ሆኖ የተዘጋጀ ነው።"የኢትዮጵያ ዘመናዊ የህፃናት የውጭ ንግድ"

EPRP: Interview with EPRP youth: ለጥያቄዎቻችሁ ሁሉ መልስ

http://www.youtube.com/watch?v=TuS6DiSOvxY&feature=youtu.be

Thursday, November 29, 2012

Tidligere norsk asylsøker skal ha blitt arrestert i Uganda

Asylsøkeren Simon Rutarondwa valgte selv å sette seg på flyet hjem til Uganda i vinter, da han hadde fått endelig avslag på asylsøknaden sin. Nå skal han sitte bak lås og slå i hjemlandet, ifølge nettstedet Chimpreports. Ifølge nettstedet er Rutarondwa tidligere asylsøker til Norge, noe også en representant for hans parti i Norge bekrefter overfor VG Nett:

- Han ble arrestert og tatt med til spesialenheten for etterforskningssaker sitt hovedkvarter i Kireka, en forstad i Kampala. Der ble han torturert og anklaget for å ville styrte regjeirngen i Uganda. Siden har han blitt siktet for forræderi og terrorisme og sitter nå fengslet, sier Samuel Makokha, representant for partiet Forum for Democratic Change i Norge. Lese mer fra:http://www.vg.no/nyheter/innenriks/artikkel.php?artid=10048273

Quote of the Week: Knowing your enemy and yourself


[Sun Tzu  in “The Art of War “ (translated by Luo Zhiye)]: 
“So it is said that if you know both the enemy and yourself, you will  fight a hundred battles without any danger of defeat; if you are ignorant of the enemy but only know yourself, your chances  of winning and losing are equal; if you know neither the  enemy nor yourself, you will certainly be defeated in every battle…read more from http://articles2u.wordpress.com/2012/11/20/quote-of-the-week-knowing-your-enemy-and-yourself/
በራስ አሉላ አባነጋ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ዜናዊ ተቀየረ Print E-mail
ኢየሩሳሌም አርኣያ
በትግራይ ተምቤን - አብዪአዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።
http://www.ethiopiazare.com/the-news/latest/2661-eyerusalem-areaya
በደል የረሳል ወይስ ይለመዳል ወገን? አንዳንዶች ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ለማገልገል እድሜ ዘመናቸውን እንደጣሩ፣ እንደፈለጉ፣ እንደናፈቁ ሳይሳካላቸው ያልፋሉ። በሌላ በኩል ሌሎች ደግሞ ይህ ወረወቃማ እድል ያለጊዜው እጃቸው ላይ ወድቆላቸው ያላግባብ ያለምንም ጥቅም ሲያሳልፉትና የወገንና የታሪክ ተጠያቂ ሲሆኑ እንመለከታለን። ሙሉውን ላማንበብ http://www.ethiopiazare.com/articles/opinion/2662-bedel-by-yehenew-anteneh

Wednesday, November 28, 2012

የቀድመዋ እመቤት ጋሻ አነሱ!

ባትወጋ ፡ እንኳን፡ በል፡ እንገፍ፡ እንገፍ፤
የአባትህ፡ ጋሻ፡ ትኋኑ፡ ይርገፍ።
 


ይህ ለዳተኛ ልጅ የአባቱን ጅግንነት ላልተከተለ ጋሻውን ለማንሳት ላልደፈረ የተዜመ
ዜማ ነበረ። የቀድመዋ ቀዳማዊት እመቤት ባለቤት አቶ መለስ ዜናዊ አዜብ መስፍንን
በፓራላማቸው ላይ ‘ቆራጥ ታጋይ’ ሲሉ አወድሰዋቸው ነበር።የዳኛ ብርቱካን መዴክሳ
በታጋይነታቸው ሰማቸው በኢትዮጵያዊያ ዘንድ እየገነነ መምጣቱ፤ የባለቤታቸውን
ታጋይነት ሰለአጠላበት ነው በቁጭት የተናተሩት ያሉም ነበሩ። የወያኔ ተጋዳዮችም
ቀዳማዊት እመቤትን እንደ ( Popular Front for Liberation of Palestine)
‘የፍልስጤም ሕዝባዊ ነፃነት ግንባር’ አባል የሆኑትን የእውቋንና ዝነኛዋን ሌዕላአ
ካህሌድ (Leila Khaled) እንደ አስራ አምስተኛው ምዕተ ዓመት ዝነኛ ፈረሳዊት
ጅግኒት የካቶሊክቱ ቅድስት ጆኖ ኦፍ አርክ (Joan of Arc) ጋር ያመሳስሏቸዋል።
በተለይ ራሳቸው ላይ ጣል የሚያደርጓት ሻሽ መሰል ኮታ ቁርጥ ሌዕላአ ካህሌድን
አስመስሏቸዋል። (AK 47) ክላሽስኮብ ይዘው ፎቶ ተነሰተው በኢቲቪ
ባለመቅረባቸው ጅግንነታቸው አልታወቀም።አፈሩን ገለባ ያድርግላቸውና ባለቤታቸው
ቢሆኑ የአርጀቲናዊን ማርክሲስት ቼ ኮቬራ (Che Guevara) መለያው የሆነችውን ቆብ ደፋ ያደርጉ ነበር።

ይህ ከውጪ የተጨለፈ የትግል ስልት ‘የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር’ (ሕውሃትን) ፈጥሮልናል። በቅርቡ የድርጅቱ መስራች አቦ ሰባት ነጋም እንደነገሩን ትግራይን ለማስገንጠል ሣይሆን የአማራውንና የኦርቶዶክ ሃይማኖት ተከታዩን የኢትዮጵያ ሕዝብ አከርካሪ ለመስበር መሆኑን ነው። ይህ ሁኔታ በልጅነቴ የሚነገር ተረት አስታወሰኝ። ጦጢት ሰው የሚያደርገውን በመኮረጅና መስሎ ለመታየት በምታደርገው ተግባሯ ትታወቃለች ። በዕውቀት ደከም ያሉትን የሕብረተሰቡን ክፍል በማታለልም ወደር የላትም። በተለይ የገበሬውን ምርት አታላ በመብላት ሌሎች
እንሰሳት አይደርሱባትም። የሚያሸንፋት ተማሪ ብቻ ነው ተብሎ ይነገራል። ከዕለታት አንድ ቀን ተማሪው ጦጢት ወደአለችበት በመሄድ ከምታየው ከፈተኛ ሥፍራ ላይ ቆሞ፣ ቢላዋ አንስቶ፣ በደነዙ በኩል ማጅራቱ ከገዘገዘ በኋላ ቢላዋውን ይወረውርላታል፤ ጦጢትም ቢላዋውን አንስታ በደመ ነፍስ በስለቱ በኩል ማጅራቷን ትገዘግዛለች ፣ ደሟ ሰዥረዥር፣ እሪ ብላ ትጮሃለች፤ ተማሪው ሊረዳት ቢሞክርም ወደ ዱሯ ትነጉዳለች ። ይህ የጦጢት ታሪክ አዲሱንም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝንም ይመለከታል።

ወደ ዋናው ወደተነሰሁበት አርዕሰት ልመለስ፤ በተጋዳይ አካባቢ የሚፈከረው መፈክር ‘ጓድ ቢሞት ጓድ ይተካል’ ነውና ወይዘሮ አዜብ መስፍን የሟቹን ባለቤታቸውን ጋሻ አንስተዋል። አነሳሳቸው ስዕላዊና ታሪካዊ ነው። አለባበሳቸው ጥቁር በጥቁር ነው፤ የትግል ጉዞቸውን ለማያውቁ ለባላቸው ሐዘን የለበሱት ነው ብለው በየዋህነት ሊገምቱ ይችላሉ። ጥቁሩ መስከረም( Black September) (Leila Khaled) ሌዕላአ ካህሌድ አባል የሆነችበት የፍልስጢም ድርጅት አርማ ነው። ታጋይቱ በዚህ ዓይነት አለባበስ ይታወቃሉ። በታጋይ ነኝ አለባበስ ቀዳማዊት እመቤት በቲቪ መስኮት ብቅ በማለት ‘መለስ የትግራይ ክልል በኢንዱስትሪ ለማሳደግ የነደፈውን ጹሑፍ ስላለ ያንን
በሥራ ላይ አውላለሁ’ ብለውን እርፍ አሉት። ይታያችሁ አዜብ መስፍን የፓርላማ አባል ናቸው። ባለቤታቸውም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመባል ነበር የሚታወቁት፤ መግለጫቸውን ስንሰማ የትግራይ ብቻ ተጠሪ ሆኑ ብለን አዘንን። በባለቤታቸው የቀብር ሥነሥረዓት ላይ ‘ከኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ ሐብት የለንም’ ብለውን ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሥልጣን ስላጡት ወደ ትግራይ ኮበለሊ ያሉም አሉ።

ሌሎች እንደሚሉት የተመረጡበትን ፓርላማና አዲስ የተሾሙትን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ላይ ጦርነት ማወጃቸው ነው የሚሉም አልጠፉም። ያም ሆነ ይህ አዋጃቸውን በቁምነገር ወስደነው የትግራይ ክልል በኢንዱስትሪ አድጎ ‘በትግራይ የተሠራ’ የሚል ዕቃ በገዛን ባልከፋን ነበር። ከሃያ ዓመት ቀደም ብሎ ቢያንስም ቢያድግም ለፍጆታ የሚስፈልጉንን ቁሳቁሶች ማምረት ችለን ነበር። ዛሬ ግን ለወጥ ማማሳያ፣ ለቡና
መቁያ፣ ለምግብ ማብሰያ፣ የምንለብሳቸው ልብሶችና ጫማዎች ሳይቀሩ በቻይና የተሠሩ ናቸው። ይህን ያየ በአገራቸን በሆነ ክልል ውስጥ ዕቃዎች ቢመረቱ፣ ጥጃ ጠባ ሆድ ገባ ነበር።ግን ቁምነገሩ ያ! አይደለም። ለትግራይ ሕዝብ ሲዋሽለት የነበረውን የመገንጠል አጀንዳ ፉርሽ መሆኑ ነው። በትግራይ ማስገንጠል ስም ለኤርትራ መገንጠል፣ በመቶ ሺ የሚቆጠር የትግራይ ወጣት አውደ ጦርነት ላይ ተማግዷል።

አቶስባት ነጋ ‘አማራውንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዩን አኮታኩተነዋል’ እንደሉትም አይደለም። በመቶ ሺዎች ያለቁበትም ባድሜ የትግራይ ክልል ሆኗል ሲባል፤ ሐቁ የኤርትራ መሆኑ ነው። በሕውሃት ወያኔ መሪነት ያጣነው የባሕር በር እስከዘለቄታው እንደማናገኘው በቅርቡ በረከት ስምዖን በአደባባይ ግልጽ አድርጎታል። ትግራይን በኢንዱስትሪ የማሳደጉ ውዥንብር ይህን ሁሉ ጥፋት ይሸፍነው ይሆን? የአልሞት ባይ ተጋዳዮች የጥቂት የትግራይ ጉጄሌዎች ማወናበጃና ጊዜ መግዣ እንጅ ፋይዳ ያለው ነገር አይደለም። ኢንዱስትሪ በትግራይ ውስጥ ለምን ተገነባ ብሎ እንቅልፍ አጥቶ የሚያድር ኢትዮጵያዊ የለም። በትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ስም በመላው ሃገሪቱም ሆነ በትግራይ ሕዝብ የተፈጸመው ግፍ ታሪክ ሲያወሳው የሚኖር ነው።ዙሪያ ጥምጥም ከሚሄድ ይልቅ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ያቆራረጡትን ቆምንለት የሚሉትን የትግራይን ሕዝብ በአደባባይ ይቅርታ ይጠይቁት። ኢንዱስ ትሪው ይቋቋም ቢባል እንኳን ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከኢፈርት ገንዘብ ወጪ፣ አድርገው ነው ወይስ ከክልሉ ግብር አስከፍለው? ከመላውየኢትዮጵያ ሕዝብ እንደይሉ ፓርላማው አልመከረበትም፤ ያም ግልጽ አልሆነም። እያደር እንደሚታየው ወይዘሮ አዜብ በዋናነት የሚቆጣጠሩትን የኢፈርት ንብረት የራሳቸው አድርገው ከሆነ ያ ሌላ ነው። ወታደር ሊቀጥሩበት ይችላሉ። ኢንዱስትሪ የተባለው ሽፋን ነው።

በአሁን ጊዜ በወያኔ አምባ የሚታየው መደነባበር እንጂ ልማት አይደለም። ወይዘሮ አዜብስ ቢሆኑ የትኛው ብቃታቸው ነው? ኢንዱስትሪ ለማቋቋም የሚረዳቸው? ከአጥፍቶ መጥፋቱ አዝማሚያ ተቆጥበው፣ የባለቤታቸውን ሐዘን በወግ ቢወጡት ይሻላል።በለቅሷቸው ላይ ‘አልጋው ባዶ ነው’ እንደሉት የሉምና ካልጋዎ ወርደው ሰሌን አንጥፈው ማቅ ለብሰው መጸለዩ ባህላዊም ሃይማኖታዊም ነው። ከእንግዲህ ምን ዓለም አሎት? ግማሽ አካሎን አተዋል፤ ከዋልድባ ገዳም ቆብ ደፍተው መመልኮሱ ይብዛቦ? ወልቃይት ጤገኔም ቢሆን የአባቶ ሃገር ነው፤ ግን ‘ ሰው ከሚጠጣው ወኃ ምራቁን አይተፋም’ በማለት ያማርሮታል፤ የዋልድማው ገዳም ጉዳይ ገና አልተቋጨም።የኢትዮጵያ ሕዝብም ቢሆን አዝኖቦታል። ከገንዘብ ዘረፋው እስከ ቡቃቅላ ወጣት ሴት ልጆቹን ለአረብ አገር ማሻገሩን እንደባሪያ ፈንጋይነት ቆጥሮታል።

የሚያነሱት ጋሻ የገንዘብ ፍቅርን፣ የእርኩስ መንፈስን፣ የሥልጣን ጥማትን የሚመክት መሆን አለበት።
ኢትዮጵያንና ልጆቿን ዓምላክ ይታደጋቸው። አሚን!
ታደለ መኩረያ
tadele@shaw.ca