1ኛ.ኢትዮጵያ ሀገራችን የብዙ ሺህ ዓመት አኩሪ ታሪክ ያላት እና የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገርባት ፣ህዝቦ የቋንቋ ልዩነት ሳይገድበው አንዱ ከሌላው የተዋለደ፤ እጅግ ውብ እና ማራኪ ቋንቋ ፣ብህል ፣ልምድ፣ ወግ ፣አለባበስ እና አመጋገብ ወዘተ… የሚታይባት ድንቅ ሃገራችን ናት፡፡ ይሁን እንጂ የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘ ለዚያውም በ21ኛ ክፍለ ዘመን አንድ ከሚያደርገን ኢትዮጵያዊነት በላይ የምንናገረው ቋንቋ እና የተወለድንበት አካባቢ መሠረት ያደረገ ጠባብ ጎሰኝነት ጎልበት እንዲኖረው ለማድረግ እየሞከረነው፡፡ ከዚህም በላይ በጎሣ መከፋፋሉ ሲያስቆጨን ይበስ ብሎ እናተ ከዚህ ቦታ ለቃችሁ ሂዱ! ይህ የእናንተ ቦታ አይደለም በማለት ዜጎችን ማፈናቀል፣ መግደል ፣ሀብት ንበረት ማውደሙ እና ዘረኝነትን ማስፋፋቱ ያላስቆጨው ያላንገበገበው ማነው ? ይህን ቁጭቱን እና በደሉን መግለፅ የማይፈልግ ማነው?
2ኛ. በዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ እምነቶች መካከል ክርስትና እና እስልምና ዋንኞቹ ናቸው፤ እነዚህን እምነቶች በመቀበል እኛ ኢትዮጵያዊያን ከቀዳሚዎቹ መካከል እንገኛለን፤ ክርስትናን እና እስልምና እምነቱን መቀበላችን ብቻ ሣይሆን የተቀበልነው እምነት ህግና ሥርዓት አክብሮ በማስከበር ወደር አይገኝልንም፡፡ በእነዚህ ታላላቅ እምነቶች መንግስት እጁን በማስገባት የፖለቲካ ዓላማ ማስፈፀሚያ ለማድረግ ያልፈነቀለው ድንጋይ ምን አለ ? በተለይ በሙስሊሞች ላይ እየፈፀመ ያለው በደል እና በእምነቱ ተከተዮች (የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች) ላይ ያለጥፋታቸው በሐሰት በመወንጀል አሸባሪ ብሎ በእስር ማሰቃየቱ እጅን አስጨብጦ ጥርሱን ነክሶ ያልተቆጨ ማነው?
3ኛ. አንዶአለም አራጌ፣ ናትናሄል መከንን፣ በቀለ ገራባ፣ ኦልባና ለሊሳ እና ሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች እንደማንም ኢትዮጵያዊ የራሰቸው ንሮ እና ህይወት ያላቸው ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ነፃነት እና ፍትህ ለነሱ ሁለተኛ ጉዳይ አይደለም የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ነው! ከራስ ወዳድነት አልፈው ይህ ጥያቄ የኛ ብቻ ሣይሆን የኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው በማለት በአደባባይ ስለነፃነት እና ፍትህ የዘመሩ በዚህም አኩሪ ተግባራቸው በእኛ የኢትዮጵያዊያን ዘንድ ልዩ ቦታ የምንሰጣቸው ነን፡፡ ይሁን እንጂ የወያኔ መንግስት እነኚህ ምርጥ የኢትዮጵያዊያን በማሰር እያሰቃያቸው ይገኛል፤ ይህ ስቃያቸው ያልተሰማን ከዚህ ስቃይ እንዲወጡ ምን ባደርግ ይሻላል እያልን እራሳችንን ያልጠየቅን ስንቶቻችን ነን ? በሆነው ነገር ያልተቆጨ ማነው ?
4ኛ. በሀገር እና በህዝብ ላይ የሚፈፀም በደል ማቆም አለበት፤ መንግስት እየወሰዳቸው ያለው እርምጃ የዜጎች ሰብአዊእና ዲሞክራሳዊ መብቶችን የጣሱ ናቸው በማለት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው ከምንም በላይ የጋዜጠኝነት ስነምግባር ጠብቀው ሚዛናዊ መረጃ ለእዝብ ያደረሱ ዓለም ዓቀፍ ተሸላሚ የሆኑ ጋዜጠኖች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ እርዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ በስራቸው ዓለም ያደነቃቸው አድናቆቱም በሽልማት የታጀበ መሆኑ ለማናችንም ግልፅ ነው፡፡ እነዚህ የዓለም ህዝብ ቆሞ ያጨበጨበላቸው ጋዜጠኞች የወያኔ መንግስት በሽብርተኝነት ወንጅሎ በማሰር እያሰቃያቸው ይገኛል ፡፡ ይህ አይቶ ወይም ሰምቶ ዝም ማለት እንዴትስ ይቻላል ?
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት አራት (4) ዋና ዋና ሃሳቦች ሀገርን እና ህዝብን የሚወድ ከምንም በላይ ለራሱ አላፊነት የሚሰማው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይህን በደል እና ግፍ የሚፈፅመውን አካል መጠየቅ እንደዚሁም እነዚህ በሐይል የተያዙ የኢትዮጵያ ልጆች እንዲለቀቁ መጠየቅ የሞራል ግዴታ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ለራሱ ሲል የሚያደርገው ነገር ነው ፡፡
ወዳጆቼ መቼም ምን ለማለት እንደፈለኩ ግልፅ ይመስለኛል ፤የፊታችን እሁ ድግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው የተቃውሞ ሠልፍ ቦታው ተገኝተን በአደባባይ ስለነፃነት እና ፍትህ ድምፃችን ከፍ አድርገን በህብረት እንዘምር !!! የዕለቱ ፕሮግራም ሰማያዊ ፓርቲ ማዘጋጀቱ እርግጥ ነው ቁም ነገሩ ግን ፓርቲው ያነሳው የህዝብ ጥያቄ ነው ! በህዝብ ላይ ደግሞ በደል እና ግፍ እየደረሰ ነው ይህ በደል እና ግፍ አይመለከተኝም ብሎ የቀረ ቀረበት፡፡