Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Friday, September 6, 2013

አቶ አሊ ሁሴን የኢፖእአኮ (SOCEPP) ፕሬዚዴንት በኦስሎ፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ እሥረኞች አንድነት ኮሚቴ ፕሬዚዴንት አቶ አሊ ሁሴን ቅዳሜ ኦገስት 31, 2013 ነበር
ከለንደን በመለስ ወደ ኦስሎ ጎራ ያሉት። በዚህ ተጋባዥ ሙስሊምና ክርስትያን ኢትዮጵያን በተገኙበት ስብሰባ
አቶ አሊ ሁሴን በሰብዓዊ መብት ዙሪያ በተለይ በወቅቱ በወያኔ እየተደርገ ባለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ በተለይ
በሙስሊም ወንድሞች፣ እህቶችና አረጋውያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የእምነት መብት ጥሰት እንዲያም ሲል
ወከባ፣ ጭፍጨፋና ግድያ በማውገዝ ችግሮችንና መፍትሔዎችን የጠቆመ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ትንተና በመስጥት
በታዳሚው ዘንድ ድብልቅልቅ ያለ ስሜትን የፈጠረ ሳቅና ለቅሶን ያፈራረቀ፣ የእሥርቤት ትውስታዎችን ብሎም
የጨካኝ አረመኔዎችን ተግባር ምን ይመስል እንደነበር ያሳየ ታርካዊ ምሥክረንትን የሰጡበት መድረክ ነበር

ከዚህ ቀደም የኢሕአፓ አመራሮች ደብዛቸው በመጥፋቱ ምክንያት የዛሬ 18 ዓመት የተመሰረተው
የኢትዮጵያ ፖለቲካ እሥረኞች አንድነት ኮሚቴ እስካለንበት ጊዜና ሰዓት በስብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ የማይናቅ
አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸው በሴቶች እህቶች ከብር ላይ ያተኮረ ግጥም ለቤቱ አቅርበዋል። ከዚያም በመቀጠል
ኢትዮጵያ ውስጥ በእርግጥ አክራሪ አሸባሪ አለ ውይ? የሚል ጥያቄ ለታዳሚው ወርውረው ሴቶቻችን አይማሩ፣
ክርስቲያኑን ጨፍጭፉ፤ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ በሻሪያ ሕግ የተዳደር ብለዋል??? አላሉም። ታዲያ እስቲ አንድ
ምልክት ስጡኝ፡ ሲሉ ቤቱ በዝምታ ድባብ ከመዋጥ በቀር የሰጠው መልስ አልነበረም።
http://www.eprpyl.com/resources/Ali%20hussien%20in%20oslo.pdf