ገለታው ዘለቀ
ከኣመታት በፊት በምርጫ ዘጠና ሰባት ኣካባቢ ኣዋሳ ከተማ ውስጥ የገጠመኝ ነገር ትዝ ይለኛል ። በኣዋሳ ከተማ ቆይታየ ጊዜ ከኣንድ ታዋቂ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ እሳተፍ ነበር። በዚህ ድርጅት መሳተፍ እንደጀመርኩ ብዙም ሳልቆይ የወጣቶች ጉዳይና የድርጅት ጉዳይ ሆኘ ተመደብኩ።ታዲያ በዚያ ኣጭር ጊዜ ቆይታየ የመንግስትን የስለላ ስራና ተፈጥሮ እንድረዳ እድል ስለሰጠኝ ያ ጊዜ ኣስተማሪየ ሆኖ ይሰማኛል ። በውነት ለመናገር ያ የኣዋሳ ቆይታየ ስለ ወያኔ ያለኝን መረዳት ኣራምዶት ነበር።
ዛሬ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (TPDM) መሪ የነበረው ኣቶ ሞላ የተወሰኑ ታጋዮችን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ገባ የሚለው ዜና ከተሰማ በሁዋላ ያ የኣዋሳው ትዝታየ የኋሊት በምናብ ታወሰኝ። በተለይም የኣቶ ሞላ ኣስገዶምን ኢንተርቪው ሳይ “እኛ ከመንግስት ጋር ስንሰራ ቆይተናል። ግንኙነት ነበረን” ሲሉ የኣዋሳ ገጠመኘን በጣም ኣጉልቶ ኣሳየኝ። Pease read more about by clicking here