ሱሉልታ የደረሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ አራት ኪሎ ይደርሳል በሚል ፍራቻ በሰሜን አዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ ክልል የተነሳውና የተቀጣጠለው የሕዝብ ቁጣ ሱሉልታ መድረሱን ዘ-ሐበሻ ቀደም ብላ መዘገቧ አይዘነጋም:: ሕወሓት የሚመራው መንግስት ሂሊኮፕተር ጭምር በማንቀሳቀስ ሱሉልታን ሲያምስ የዋለ ሲሆን ሕዝቡም የጎጃም መንገድን ዘግቶ እንደነበር ይታወሳል::
የሱሉልታው ሕዝባዊ ቁጣ አዲሱ ገበያ ከዛም አልፎ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ይደርሳል ብሎ የሰጋው መንግስት ዛሬ በአዲስ አበባ ሰሜናማው ክፍል የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ዘግቷል:: በተለይ ቀኑ አርብ በመሆኑና ቅዳሜና እሁድም በአዲስ አበባ ትምህርት ስለማይኖር እፎይታን አገኛለሁ ብሎ ያዳመረው መንግስት በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ይገኛል ተብሏል::
እንደ ዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ከሆነ ከሱሉልታ ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ የመኪና ጉዞዎች ከተቋረጡ 2 ቀናቸውን የያዙ ሲሆን በመንግስት ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫናን ፈጥሮበታል:: ከአዲስ አበባ በሱሉልታ በኩል የሚያልፉ መንገዶችም ከተዘጉ እንዲሁ 2ኛ ቀናቸውን አስቆጥረው ሶሰስተኛቸውን ይዘዋል::
በአዲስ አበባ በማንኛውም ጊዜ ሕዝባዊ ቁጣው ይነሳል ተብሎ እየተጠበ ነው:: Source from http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49233