ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በኢትዮጵያ መንግስት አማካኝነት እየተፈጸመባቸው
ያለውን ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመተቸት መግለጫ ያወጣው የአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ የሃይማኖት
ነጻነት ኮሚሽን ልኡካን አባላት ትላንት
ኢትዮጵያ
መግባታቸው ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ኮሚሽኑ አውጥቶት በነበረው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በኢስላማዊ የሃይማኖት
ተቋም (መጅሊስ) ውስጣዊ አመራር ውስጥ ያልተገደበ ጣልቃ ገብነት ማሳየቱ፣ አዲስ አስተሳሰብ (አሕባሽ) በሙስሊሙ
ኅብረተሰብ ላይ ለመጫን መሞከሩ፣ በርካታ ኢማሞችም በዚሁ ሰበብ ከኢማምነት መነሳታቸው፣ መንግስት በአዲሱ የመጅሊስ
ምርጫ ላይ ያልተገደበ ጣልቃ ገብነት መፈጸሙን አስረግጦ መግለጹ ይታወሳል፡፡
To read more visit Walilign mekonen (ዋልልኝ መኮነን) webseit
No comments:
Post a Comment