Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Wednesday, August 12, 2015

ባራክ ኦባማ! ምነው እውነቱን ብትናገር ስለ ኢትዮጵያ

August 6, 2015
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ማስጠንቀቂያ!
አቁም!
ስለ ባራክ ኦባማ እውነት ማወቅ ካልፈለግህ ይህን ጦማር ማንበብ አቁም። “እውነትን ለሚጠሉ ሁሉ እውነት ጥላቻ ይመስላቸዋል፡፡”
“ምላሴን  ብቆነጥት አምሮየን ያመዋል!”
ባራክ ኦባማ መላስህን ቆንጥጥ !
ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን በጎበኘበትጊዜ የሚከተለውን መግለጫ በመስጠት በርካታ ህዝቦችን አስደንግጧል፡obama-ethiopia-speech
“ወደእነዚህ ጉዳዮች በሚመጣበት ጊዜ እጅግም  ምላሴን አልቆነትጥም ፡፡ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግስት ጨምሮ ኃይልን በመጠቀም ከስልጣን ለማስወገድ ጥረት የሚያደርግን ማንኛውንም ቡድን አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ ይህች ሀገር ያለፈችባቸውን ፈተናዎች ሁሉ ከግንዛቤ በማስገባት የኢትዮጵያን ታሪክ በጥንቃቄ እንከታተላለን፡፡ ሕገ መንግስት ተረቅቆ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ምርጫ እየተካሄደ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ስልጣን የያዘበት ጊዜ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቅርብ መሆኑም አናውቃለን ፡፡”
እውን በኢትዮጵያ ያለው መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነውን!?!
ባራክ ኦባማ ምን ለማለት እንደፈለገ  ሀሳቡን ግልጽ ቢያደርግ !!!
እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 በኢትዮጵያ ከህዝብ ፈቃድ ውጭ በጠብመንጃ ኃይል በስልጣን ኮርቻ ላይ ተንጠልጥሎ የሚገኘው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ አካሂዶ ነበር፣ እናም የቅርጫ ምርጫውን መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብሎ አይን አውጥቶ አውጇል፡፡
አምባገነኑ የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንገን እንኳ እ.ኤ.አ መጋቢት 2014 ተካሄደ በተባለው ፓርላሜንታዊ ምርጫ መቶ በመቶ በማሸነፍ የምርጫ ድልን ተቀዳጅቻለሁ ለማለት አልደፈረም ነበር፡፡
ቢያንስ በወረቀት ላይ የኪም ጆንገን “የሰሜን ኮሪያው የሰራተኞች ፓርቲ” 88.3 በመቶ (ከ687 መቀመጫዎች ውስጥ 607 መቀመጫዎችን በመያዝ) ብቻ ማሸነፉን ገልጾ ነበር፡፡
“የኮሪያ ሶሻሊስት ዴሞክራቲክ ፓርቲ” 50 መቀመጫዎችን አሸንፎ ነበር፡፡ እንደዚሁም ደግሞ “የቾንዶይስት ቾንጉ ፓርቲ” 22 መቀመጫዎችን አሸንፎ ነበር፡፡ በጃፓን የሚኖሩ ጠቅላላ ኮሪያውያን ማህበር/General Association of Korean Residents in Japan ደግሞ 5 መቀመጫዎችን አሸንፎ ነበር፡፡ በሌላ በኩልም የኃይማኖት ማህበር/Religious Associations የተባለው ፓርቲ 3 መቀመጫዎችን አሸንፎ ነበር፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ “በምርጫ በንቃት የሚሳተፉ” 79 የተመዘገቡ እና ሕጋዊ ህልውና ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ አየተባለ ይለፈፋል፡፡
እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ)/Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) እየተባለ የሚጠራው ግን የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/Tigrean People’s Liberation Front  እያለ አራሱን የሚጠራው  ፈላጭ ቆራጭ ድርጅት መደበቂያ  ግንባር  የሚመራው የይስሙላ ስብስብ ድርጅት ለይስሙላ  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ከ547 መቀመጫዎች ውስጥ 547ቱንም ጠቅልሎ በመውሰድ ማለትም መቶ በመቶ አሸነፍኩ በማለት አወጀ፡፡ Please read the four pages article "President Obama's tell the truth about Ethiopia" wrote in amharic from the link http://ecadforum.com/Amharic/archives/15471/

No comments:

Post a Comment