Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Thursday, March 23, 2017

እምባ በተቀነባበረ ህዝባዊ እምቢተኝነት መተካትአ ለበት (ከአለም ማሞ)

ከአለም ማሞ
“….ብቸኛ ምሬት ነው ሃይሉ ወኔ መስለቢያው ነው እምባ ……” 1
ከሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን “ የቴዎድሮስ ስንብት ከመቅደላ” ግጥም የተወሰደ
ከመከረኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በዘረፉት ሃብት ንብረት ጠግበው የሚያቀረሹት የህወሃት/ ኢሕአዴግ የጥፋት መልእክተኞች በዚህ ባለፈው ሳምንት የትውኪያቸው ጎርፍ ገደብ ጥሶ በወገኖቻቻን ላይ ያደረሰው የሞትና የመቁሰል አደጋ በአገራችን ላይ ለሃያ ስድስት አመታት ያለማቋረጥ የሚደርሰውን ብሄራዊ ውርደት እጅግ አሰቃቂ ደረጃ ላይ አድርሶታል። ህጻናት አዛውንት ወጣቶች ሴቶችና ወንዶች የቆሻሻ ክምር ተንዶባቸው ህይወታቸውን ሲያጡና ለአካል ጉዳት ሲዳረጉ ማየት ዘግናኝነቱ ስብእና ለሚሰማው ልብ ሁሉ በጽኑ የሚያም ነው። አንድ በእድሜዬ ከፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ጀምሮ “ ሁሉን አይቻለሁ” የሚሉ የአዲስ አበባ ነዋሪ አዛውንት እንዳሉት “ ከዚህ የከፋ ብሄራዊ ውርደት አይመጣብንም። በቆሻሻ ዙርያ መኖሪያቸውን ያደረጉ ወገኖቻችን መኖር ከተከለከሉ ከእንግዲህ በዚህች ምድር መኖር ምን ትርጉም አለው?” ሲሉ በምሬትና እንባ በሚተናነቀው ድምጽ ተናግረዋል።Ethiopian garbage dump landslide
አዎ ንዋያዊ ድህነትና ከዚያ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የነበሩ ያሉና ወደፊትም የሚኖሩ ናቸው። እኛ ኢትዮጵያዊያን በሃብትና በቴክኖሎጂ ከዳበሩ ሃገሮች ጋር ስንወዳደር ብዙም ሚዛን የሚደፋ ደረጃ ላይ አይደለንም። እንደ አገርና እንደ ህዝብም በውጫዊና በውስጣዊ ምክንያቶች በርካታ ፈተናዎችና መሰናክሎች ተቋቁመን አልፈናል።አንድም ጊዜ ግን በዚህ ደረጃ ብሄራዊ ውርደት ደርሶብን አያውቅም። የህወሃት/ኢህአዴግ ግፈኛ አስተዳደር በውጭ ወራሪ ከሚደርስ ግፍ በመረረና በከፋ ሁኔታ አገራችንን ህዝቡንም እያዋረደና እያሰቃየ መግዛቱን ቀጥሎበታል። ይህ በተለምዶ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢም የደረሰው ሰቆቃም የዚህ ስርአት አመታት ያስቆጠረ ጭቆናና ምዝበራ ውጤት ነው።
Please read more from http://ecadforum.com/Amharic/archives/17506/

No comments:

Post a Comment