Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc
ወያኔን ማስገደድ ወይም ማስወገድ የሞራልና ተፈጥሮዓዊ ግዴታ
ወያኔ/ኢህአዴግ የሰላማዊ በሮችን ሁሉ በመዝጋት በሀይል እየገፋና እየደፈጠጠ ስለ ሰላም የሚያወሩትን፣ ነጻነት
የሚጠይቁትን፣ እንደወንጀለኛና ሽብርተኛ ታርጋ እየሰጠ ዴሞክራሲን ማፈኑ፣ ነጻነታችንን መግፈፉና የፖለቲካውን ምህዳር
ማጥበቡ፤ የሀገራችን ህዝብ ሆ! ብሎ የተዘጋውን የሰላም በር ለማስከፈትና እንደ አረቡ አለም ጸደይ አቢዎት
ተባብረን ስርአቱን የምናስወግድበት ቀን ሩቅ አይሆንም።
ሰሞኑንንም በኢትዮጵያ የሚገኙ ተቃዋሚ
ፓርቲዎች ይኼው የሰላሙ ትግል ተዳፍኖባቸው ለቀበሌና ለወረዳ ማሟያ በሚደረገው ምርጫ አንሳተፍም ብለዋል። ወያኔ
ለዚህ ሁሉ ህዝብን ወደ አላስፈላጊ አማራጭ መግፋቱ አሁንም በታሪክ ተጠያቂ ያደርገዋል። በእኛ እምነት በሰላማዊ
መንገድ የሚፈታ ማናቸውንም አማራጭ ሀሳቦችን ወደ ጠረንጴዛ በማምጣት መወያየት ስልጡን የሆነ፣ ስልጣን የህዝብና
በህዝብ የሚመጣ መሆኑን ማረጋገጫ ስለመሆኑ አሁንም ደግመን ደጋግመን እንናገራለን። የበለጠ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጠቁሙ
No comments:
Post a Comment