ለነጻነት
መዘመራችን
ስለ
ሃቅ መናገርችን
ስለፍትህ
መጻፋችን
ኣስከፍቱዋቸው
ከሃዲወችን
ለስራቸው
ከዳረገን
እስር
ቤት ካጎሩን
ከሞከሩ
ሊለጉሙን
የነጻነት
እንደበትን
ስሙ-ሰሚ ኣጠናክር ህብረትህን
ለማስወገድ
ፍርደ ገምዲልን።
እጠርግልህ
የለ ጎደና ኣንጽልህ የለ ህንጻ
ኣፍህን
ዝጋ ጸጥ ብለህ ተገዛ
ተመቻቹ
ለግነዛ
ማለት
ኣይቻለንም እንደዋዛ
ኣይደለንም
እና ፈዛዛ
ስሙ-ሰሚ ሁል ጊዜ
ኣትንዛዛ
እንቢ
በል ይልቅ በብልጭልጭ ኣትደንዝዛ።
ደብዛቸው የጠፋው ፀጋየም
የፕሮፌሰር ኣስራት መቀደም
የፕሮፌሰር ኣስራት መቀደም
የነ
ኣስፋ ማሩ ደም
የነህጻን
ነብዩንም
የከፍተኛ
ተማሪዋ የሽብሬም
እረ
የስንቱ ኢትዮጲያዊ ደም
በምንም
የሚተኩ እኮ ኣይደሉም።
ቤተሰብ
ወዳጁን ላጣ
ደሙ
ደመ ከልብ እዚህም ኣዛም ጋ
ግዲብ
ኣይሆን የህይወት ዋጋ
በግፍ
ለተገደለ ዜጋ
ወዳጀ
ስሙ-ስማ እረ
ኣትረጋጋ
ዛሬ
ነገ ኣትበል ተው ኣሁን ተዋጋ።
ህንፃው
እና ጎዳናው
የሰውን
ህይወት ኣይተካው
ድሃን
በማጥፋት ልማት
ስላማይችል
በግትርነት
ፍርድ
ካጣን ስለ እውነት
ስሙ-ሰሚ በፍጥነት
ለመታገል
ለመዋጋት።
ዘመድ
- ወገንን
ስማው
ፍትህ
ላጣው
ከስርቤት
ለታጎረው
ዲምፁ
ላታፈነው
መጣጥፍ ለተከለከለው
ችሎታ
እና እውቀቱ ላስገደለው
ፍትህ
ፈላጊው ጋዜጠኛው
ኣይወርዱ
ውርደት ለተዋረደው
ስሙ-ሰሚ እኛ ነን ባለ ኣደራው
እንታገል
ባንድነት ነጻ እናውጣው።
ስማ
ወዳጅ ስማ ወግኔ
እምነትህ
ሲወገዝ ሁሌ
በዚህ
እመን ሲባል እንዳልባሌ
ኣልፎ
ተርፎም ሲዘጋብን እከርቸሌ
ሲደበደብ
እና ሲሰበር እንዳኮሌ
በትውልድ
ሃገሩ ሲታዘዝ እንደ ሎሌ
ስሙ-ሰሚ ሳትል እገሊት
እና እጋሌ
ባንድ
ላይ ኣምጽ በል ያሆ ላሌ
ወገንህን
ታደግ ነው እና ነገ በኔ
ታሪክህን ዘክር በኢትዮጲያዊ ወኔ።
ስሙ-ሰሚ እንባንን እዚህም እዛም ጋ
ጠላትን ታግለነው ዛሬ እንስስጠው ዋጋ።
ተጻፈ
በኣርጋው December 30 / 2012,
Oslo - Norway
No comments:
Post a Comment