I am ambitious to see a true democracy, justice and equality particularly in Ethiopia and generally in the world.
Pages
Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc
Tuesday, March 26, 2013
ዳያስፖራው ኢትዮጵያዊ ሊመሰገን ይገባዋል!
ድምጻችን ይሰማ ተቃውሞ ያልተደረገበት የአሜሪካና የአውሮፓ ከተማ የለም ቢባል አልተጋነነም
ከዳያስፖራ ወገኖቻችን ገና ብዙ እንጠብቃለን
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሃይማኖታችን ገፍቶ የመጣብንን አደጋ ለመመከት ድምጻችንን አስተባብረን ተቃውሟችንን
ማሰማት ከጀመርንበት ቀን አንስቶ ከበርካታ ወገኖች በአይነትና በመጠን የተለያየ ድጋፍ ስናገኝ ቆይተናል፡፡ በዚህ
አይነቱ የትግል ወቅት ‹‹ድጋፍ›› ሶስት ፊደል ቃል ብቻ አይደለም - ወንድማዊ ትስስርን፣ በችግር ጊዜ የማይበጠስ
ጠንካራ ሰንሰለትን መፍጠር የሚችል ታላቅ ስጦታ ነው! ዛሬ ድጋፋቸውን ሲያበረክቱልን ከቆዩት ኢትዮጵያውያን
ወንድሞቻችን መካከል አንዱን ክፍል በምስጋናችን ልናወሳ ወደድን - ዳያስፖራውን!
ዳያስፖራው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ለትግላችን ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማበርከት
የቻለውን ሁሉ አድርጓል፡፡ እስካሁን ዳያስፖራው የእኛን ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› ተቃውሞ ያላስተጋባበት የአሜሪካና
የአውሮፓ ከተማ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ የዳያስፖራ ወንድሞቻችን ሰልፍ በርካታ ከተማዎችን አዳርሷል፡፡
ከኒውዮርክ እስከ ካናዳዋ ኦታዋ ዞሯል፡፡ ከዋሽንግተኑ ነጭ ቤተ መንግስት እስከ ስዊዘርላንዱ የተባበሩት መንግስታት
መስሪያ ቤት ደጅ ጠንቷል፡፡ የእንግሊዝ እና ስዊድን ከተሞችን አዳርሶ፣ ጀርመንን አልፎ የብራስልሱን አውሮፓ ህብረት
ቢሮ አንኳኩቷል፡፡ ፓሲፊክ ውቅያኖስን ተሻግሮ የአውስትራሊያዋን ሲድኒ ደጃፍ ረግጧል፡፡ የሰሜን አፍሪካዋን ግብጽ
ዳስሶ በታችኛዋ ደቡብ አፍሪካ ድምጹ ተሰምቷል፡፡ እስያ አህጉር ገብቶ ሪያድን ጅዳን አዳርሷል፡፡ ጥቂቶቹን እንዲሁ
ጠቃቀስናቸው እንጂ የኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች የ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› ድጋፍ ሰልፍ ያልረገጠበት ቦታ የለም!
To read more please open http://www.assimba.org/Articles/YeDiasporaw_Misgana.pdf
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment