መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ከተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ተይዘው የታሰሩ ሙስሊም
የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ፣ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ ባለማወቃቸው በቀለብ እና በልብስ እጦት እየተቸገሩ ነው።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ተማሪዎችና መምህራን ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ፣ ብዙዎቹ ቶርች ( አሰቃቂ ድብደባ) ተፈጽሞባቸዋል። በአሁኑ ጊዜ የረባ ምግብ አጥተው በመሰቃየት ላይ የሚገኙት ተማሪዎች ልብሶቻቸው በላያቸው ላይ እያለቁባቸው ለእርዛት መዳረጋቸውም ታውቋል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ተማሪዎችና መምህራን ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ፣ ብዙዎቹ ቶርች ( አሰቃቂ ድብደባ) ተፈጽሞባቸዋል። በአሁኑ ጊዜ የረባ ምግብ አጥተው በመሰቃየት ላይ የሚገኙት ተማሪዎች ልብሶቻቸው በላያቸው ላይ እያለቁባቸው ለእርዛት መዳረጋቸውም ታውቋል።
የተለያዩ ታማሪዎች በየጊዜው እየተያዙ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን በማእከላዊ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው ከሚገኙት መካከል የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆኑት ኑርየ ካሲም እና ካሊድ ሙሀመድ፣ የጅማ ዩኒቨርስቲዎቹ ያሲን ፈይሞ፣ ሙሀመድ አሚን ከድር፣ እና ጁነዲን ሁሴን፣ የሚዛን ተፈሪው አብዱላኪም አህመድ፣ የወሎ ዩኒቨርስቲዎቹ ጣሂር ሙሀመድ ፣ ሙሀመድ አብዱራሂም እና ሰኢድ ሙሀዲን፣ የጎንደር ዩኒቨርስቲዎቹ ሰኢድ አብርሀም ፣ኦማር ሙሀመድ፣ እና ሊና ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው አብዱላዚዝ ሰኢድ እንዲሁም የአዋሳ ዩኒቨርስቲዎቹ አብደላ ሙሀመድ ይገኙበታል።
የሙስሊም ጉዳይ አምደኛ የነበረው ሶሎሞን ከበደ፣ የከሚሴው ዳኢ ጀማል ከበደ፣ የሻሸመኔው ዳኢ አብዱረዛቅ ሼህ አህመድ፣ የከሚሴው ዳኢ ኢክርሀም አብዱ፣ የሀረርጌው ሁሴን ሮባ፣ የድሬዳዋው ሙሀመድ ሀሰን፣ የከምሴው ሁሴን አሊ እና አደም አህመድ አሊ በማእከላዊ እስር ቤት ታሰሩት ከፍተኛ ስቃይ ከደረሰባቸው መካከል ይገኙበታል።
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር መንግስታቸው እርምጃ እንደሚወስድ ሰሞኑን በባህርዳር በመካሄድ ላይ ባለው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።
No comments:
Post a Comment