EMF
– ትናንት ማታ ግርማይ ገብሩ (የVOAው የመቐለ ዘጋቢ ጋዜጠኛ) የህወሓት ስብሰባ ኣስመልክቶ ባጠናቀረው ዘገባ
ብርሃነ ኪዳነማርያም የተባለ የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባል በህወሓቶች የመከፋፈል ኣደጋ ስለመኖሩና ኣለመኖሩ እንዲያብራራ
ተጠይቆ ሁሌም እንደሚሉት ኣፉን ሞልቶ ‘በፍፁም የለም’ እንደ ሚል ኣልተጠራጠርኩም ነበር። ምክንያቱም መሪዎቻችን
በ1993 ዓም ‘በህወሓት መከፋፈል ኣልነበረም’ ብለው የሚከራከሩኮ ናቸው። ደግሞ ኣደጋው ቢኖርስ እንዴት ለሚድያ
ሰው ‘ኣዎ የመከፋፈል ነገር ኣለ’ ብሎ ሊናገር ይችላል? ግን ኣደጋው መኖሩ ኣልደበቀም ……. ‘ መከራከር ያለ
ነው…. ምናምን …. ዙርያ ጥምጥም …. ። እኛስ ገብቶናል፤ እናውቀዋለንም።
የመሪዎቹ ኣለመግባባት በጉባኤውም እንደቀጠለ ነው። ስብሓት ነጋ ያለ ድምፅ እንዲሳተፍ ተደርገዋል። ሙሁራን
(በተለይ ደግሞ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ኣባላት) ጥያቄ ሊያስነሱ ይችላሉ በሚል ስጋት በጉባኤው እንዳይሳተፉ ተደረገዋል
(ሁለት ብቻ ያለ ድምፅ እየሳተፉ ነው)።
የትግራይ ቡድን (የነ ኣባይ ወልዱ ማለቴ ነው) ተሳታፊዎቹ በጥንቃቄ መመልመል ችለዋል። ከ40 በላይ ከሚሆኑ
የፓርቲው ኣደረጃጀት ወረዳዎች (ከያንዳንዱ) 25 በድምፅና 1 ያለ ድምፅ በጠቅላላ ወደ 1500 የሚጠጉ ተሳታፊዎች
ኣሉ። ኣብዛኞቹ ተሳታፊዎች ገበሬዎችና በብዛት የኣንደኛ ደረጃ ኣስተማሪዎች እንዲሆኑ ተደርገዋል (ጥያቄ እንዳያበዙ
ተብሎ ነው)።
በጉባኤው ‘1ለ5’ የተባለ የፖለቲካ ስትራተጂ ተግባራዊ እየሆነ ነው። የተሳታፊዎቹ ኣቀማመጥ በየመጡበት መሰረት
ነው። ኣምስት-ኣምስት ተበድነው ይቀመጣሉ። ለእያንዳንዱ ባለ ኣምስት ቡድን ኣንድ ታማኝ (በቤተሰብና ጎጥ መሰረት)
መሪ ኣለ። እያንዳንዱን የቡድኑ ኣባል የተመደበለትን የቡድኑ መሪ ያዘዘውን ያደርጋል። ድምፅ በሚሰጥበት ግዜ
ኣባላቱ የቡድን መሪያቸው ተከትለው እጃቸው ያወጣሉ። እሱ ዝም ካለ ዝም ይላሉ።
የጉባኤው መሪዎች (Presidium) ለተሳታፊዎች ዕድል ሲሰጡ (ተመራጮች ለመጠቆም ይሁን ሓሳብ ለመስጠት)
ቀድመው ለማን መስጠት እንዳለባቸው፣ ቀጣዩ ባለ ተራ ማን እንደሆነና ማንን እንደሚጠቁም ወይ ምን ዓይነት ሓሳብ
እንደሚሰጥ ያውቁታል። ሁሉም ነገር ተደራጅተዋል። (‘የድርጅት ስራ’ ነው)። በጉባኤው ማን እንደሚሳተፍ
(እንደማይሳተፍ) በዝርዝር ተቀምጠዋል።
ለምሳሌ የጉባኤው ሰብሳቢዎች (Presidium) ሲመረጡ ‘የድርጅት ስራ’ ተግባራዊ ሁነዋል። ኣባላቱ የተመረጡት
ባለፈው ሳምንት በተደረገው ‘የኣጀንዳ መለየትና ሽምግልና’ ስብሰባ ነው (ግን ጉባኤው ሲጀመር የተመረጡ ኣስመስለው
ኣቀረቡዋቸው)። ኣመራረጣቸው ሁለት ከትግራይ ቡድን (የነኣባይ ወልዱ)፣ ሁለት ከኣዲስ ኣበባ ቡድን (የነ
ደብረፅዮን ወይ ኣርከበ) ሲሆኑ ኣንድ ደግሞ ከመሃል ሰፋሪዎቹ እንዲሆን ተሰማምተው ነበር። ኣምስቱ የተጠቆሙት
ባለፈው ስብሰባ ተካፋይ በነበሩ የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት ናቸው። ሌሎች ኣይፈቀድላቸውም። በዚ መሰረት:
ከትግራይ ቡድን
1) ኣባይ ወልዱ (ከወንዶች)
2) ኣዜብ መስፍን (ከሴቶች)
ከኣዲስ ኣበባ ቡድን
1) ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ከወንዶች)
2) ፈትለወርቅ ገ/ሄር መንጀርኖ (ከሴቶች)
ከመሃል ሰፋሪዎች
ኣባይ ፀሃዬ ናቸው።
በድርጅት ስራው የኣዲስ ኣበባ ቡድን ግራ እንደተጋባና የኣቋም ልዩነቱ በግልፅ እንደሚንፀባረክ ለማወቅ
ተችለዋል። የኣዲስ ኣበባዎቹ በጉባኤው ደስተኝች እንዳልሆኑ ያስታውቃሉ። ግን ጫና በዝተባቸዋል። “ህወሓት ጥንካሬ
ከሌለው እኛ ምን ይዋጠን ?” የሚል ተማፅኖ ከሌሎች የኢህኣዴግ ኣባል ድርጅቶች ይሰማል።
የመቐለው ዘጋቢም በመጨረሻ እንዲህ አለ፡ “የመሪዎቻችን የምሽት ቆይታ፣ የስካር ነገር፣ የዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎች
ጉዳይ …… ብቻ ይደብራል። በመቀሌ በ14፣ 15 ና 16 ቀበሌዎች በወረዱ መጠጥ ቤቶች ጎራ በሉ። በምታዩት ነገር
ትገረማላቹ። እኔ ግን ስለ ደበረኝ እዚሁ ልፅፈው ኣልቻልኩም። ብቻ ግን የመሪዎቻፍሁን ስነ ምግባር ብታውቁ ኑሮ ከኔ
በላይ እንደምትቃወሙዋቸው ኣልጠራጠርም።” ምንጭ ማጣቀሻ
No comments:
Post a Comment