Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Wednesday, January 23, 2013

ኢትዮጵያ ፣ የ ጋዜጠኞቹ ገጠመኝና ዓላማ - ማርቲንን ዮሃን


epa03040270 (FILE) A handout picture taken in 2010 and provided by Kontinent Agency on 18 October 2011 shows Swedish photojournalist Johan Persson on assignment at an undisclosed location. Reports state that a court in Ethiopia on 21 December 2011 found Persson and his colleague and journalist Martin Schibbye guilty of supporting terrorism after the pair illegally entered the country from Somalia with the rebel Ogaden National Liberation Front (ONLF). The pair now face up to 15 years in prison. Swedish Prime Minister Frederick Reinfeldt said in a statement that they should be freed as soon as possible as they have been in the country on a journalistic mission. Their next court appearance is scheduled for 27 December 2011 when sentencing could occur. EPA/KONTINGENT AGENCY SWEDEN OUT HANDOUT EDITORIAL USE ONLY/NO SALES +++(c) dpa - Bildfunk+++

ኢትዮጵያ ፣ የ ጋዜጠኞቹ ገጠመኝና ዓላማ

ማርቲንና ዮሃን ቃልቲ ሳሉ ሌሎች እስረኞች «የስዊድን ኤምባሲ» የሚል ስያሜ ወደተሰጠው መኝታ ስፍራቸው ይመጡ እንደ ነበር በፈገግታ ያስታውሳሉ። የኦጋዴን በረሃና የቃሊቲ እስር ቤት ገጠመኞቻቸውን የሚተርክ መጽሐፍ በጥቂት ወራት ውስጥ ሲያሳትሙ ገቢው በኢትዮጵያ የሚገኙ ጋዜጠኞችንና ቤተሰቦቻቸውን የሚረዳ ተቋም ለማቋቋም እንዲውል አቅደዋል፤
Pedestrians walk past the Federal High Court building in Addis Ababa, Ethiopia Tuesday, Nov. 1, 2011. A witness in a terror trial against two Swedish journalists Johan Persson and Martin Schibbye arrested during a clash with rebels in the Ogaden in the country's restive east in July told the court on Tuesday that the pair planned to support a rebel group. The two Swedes pleaded not guilty to charges of terrorism during a preliminary hearing Oct. 20 but admitted to having violated immigration laws. (AP Photo)
የኢትዮጵያ መንግስት ድንበሬን ያለፈቃድ አቋርጠዋል፣ አሸባሪዎችን ደግፈዋል በሚል ክስ ያሰራቸው ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቤና ጆሃን ፔርሰን ከእስር ከተለቀቁ አምስት ወራት አልፈዋል። ጋዜጠኞቹ በኦጋዴንና በቃሊቲ እስር ቤት ሳሉ ያጋጠማቸውን በመጽሐፍ ለማሳተም ዝግጅት ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችንና ቤተሰቦቻቸውን የሚደግፍ ድርጅትም ለማቋቋም እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ከእስር የተፈቱትን የስዊድን ጋዜጠኞች ሉድገር ሻዶምስኪ አነግሯቸዋል ገመቹ በቀለ እንደሚከተለዉ አሰባስቦታል።

ማርቲን ሺቤና ዮሃን ፔርሰን የኢትዮጵያን ድንበር በህገወጥ መንገድ በመግባትና ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ጋ ተባብረዋል በሚል ክስ ታስረው 14 ወራት በቃሊቲ እስር ቤት ከቆዩ በኋላ ነው ባለፈው መስከረም ወር ከእስር የወጡት። በኦጋዴን በረሃና በእስር ቤት ያሳለፉትን ቆይታ በመጽሐፍ የማስፈር ሐሳብን የወጠኑት እዚያው ቃሊቲ እስር ቤት ሳሉ ነው፤ ማርቲን ሺቢዬ፣

epa02970731 A handout picture taken in 2009 and provided by Kontinent Agency on 18 October 2011 shows Swedish journalist Martin Schibbye on assignment in the Philippines. The trial of two Swedish journalists, who were arrested on allegations of terrorists activity in Ethiopia's Ogaden region on 01 July after entering the country from Somalia with the rebel Ogaden National Liberation Front (ONLF), is due to start in Addis Abeba, Ethiopia on 18 October 2011. EPA/KONTINGENT AGENCY HANDOUT EDITORIAL USE ONLY/NO SALES +++(c) dpa - Bildfunk+++
ማርቲን ሽብዮ


«ለ14 ወራት የመናገር፣ የመጻፍና የማሰብ መብታችንን ተነግፈናል። በነዚህ የስቃይ ወራት ምናልባት አንድ ቀን ወጥተን ይህን ታሪክ እንጽፋለን ብለን እናስብ ነበር። እንዲህ ዓይነቱ የጋዜጠኝነት የተስፋ አጥር ነው አዕምሮአችን ንቁ ሆኖ እንዲቆይ ያደረገ።»

ማርቲንና ዮሃን አሁን ከእስር ነጻ ሆነው ሀገራቸው ተመልሰዋል። ሆኖም በቃልቲ ያሉ የሌሎች ጋዜጠኞች ህይወት አሁንም እንደሚሳስባቸው ይናገራል ዮሃን ፔርሰን፣

«በርግጥ ከእስር በመለቀቃችን እድለኞች ነን። ሆኖም ግን አዕምሮያችን እረፍት አላገኘም ምክንያቱም ብዙ ባልደረቦቻችን አሁንም እዚያው ናቸው። ብዙን ጊዜ በምን ዓይነት ሁኔታ እንዳሉ ራሴን እጠይቃለሁ። አሁንም እዚያው ናቸው። ምክንያቱም እዚያ ከገባህ ጥሩ ስፍራ አይደለም። በዚህ እስር ቤት መሞት ቀላል ነው። እኛ ከመንግስታችን ባገኘነዉ ትልቅ ድጋፍ ነጻ ወጥተናል። በርካቶች ግን አልታደሉም አሁንም እዚያው ናቸው። »



ማርቲንና ዮሃን ቃልቲ ሳሉ ሌሎች እስረኞች አስፕሪንና ሌሎች መድኒቶችን ለማግኘት «የስዊድን ኤምባሲ» የሚል ስያሜ ወደተሰጠው መኝታ ስፍራቸው ይመጡ እንደ ነበር በፈገግታ ያስታውሳሉ። የኦጋዴን በረሃና የቃሊቲ እስር ቤት ገጠመኞቻቸውን የሚተርክ መጽሐፍ በጥቂት ወራት ውስጥ ሲያሳትሙ ገቢው በኢትዮጵያ የሚገኙ ጋዜጠኞችንና ቤተሰቦቻቸውን የሚረዳ ተቋም ለማቋቋም እንዲውል አቅደዋል፤

«እዚህ ስዊዲን ትልቅ ድጋፍ አለን። ህዝቡ 170 ሺ ዩሮ አሰባስበውልናል። ይህ ገንዘብ እስር ቤት እያለን በጣም ረድቶናል። በተቀረው ገንዘብ አንድ ቀና ተግባር ለመፈጸም አስበናል። ከመጽሃፉ ሽያጭ በሚገኝ ገቢም የዮሃንና ማርቲን ተቋምን አቋቁመን፣ በዚያ አስቀያሚ ሁኔታ የሚኖሩትን ጋዜጠኞች በመድሃኒት፣ በምግብና በህግ ድጋፍ ለመርዳት አቅደናል። እናም ወደ ፊት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና ቤተሰቦቻቸው ለተቋሙ በማመልከት የገንዘብ ማግኘት ይችላሉ።»

ገመቹ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic  ለማድመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ

No comments:

Post a Comment