Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Sunday, January 27, 2013

ሰራዊታችን ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ፡ ብዛት ያላቸው ሴት ታጋዮችም ግንባሩን ተቀላቀሉ!

 
 
 
 
 
 
1 Vote

ETHflag
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ነበልባል ጦር ጥር 17-2005 ዓ.ም በወልቃይት ጎብለል በተሰኘ የወያኔው መከላከያ ካምፕ ላይ በወሰደው ድንገተኛ ማጥቃት በካምፑ የሚገኙ የመከላከያ አባላትን ደምስሷል። በውጤቱም 25 ሙት 36 ቁስለኛ እንዲሁም  20 ክላሽንኮፍ ጠብመንጃ ፣ 4 የእጅ ቦንብና 1 ስናይፕር ጠብመንጃ ከነ ሙሉ ትጥቁ በመማረክ በማግስቱ ማለትም በትናንተናው እለት በቀጠለው የነበልባል ሰራዊት ወታደራዊ ጥቃት በወልቃይት ጠበቆ በተባለ ቦታ 24 የአገዛዙ ታጣቂዎች ሙትና 29 ቁስለኛ ሆኗል። በድምሩ በሁለት ቀናት ውጊያ በጠቅላላው 49 ሙት 65 ቁስለኛ ሲሆን፦ የአምባገነኑ አገዛዝ ሰራዊት የአርበኛውን ጡጫ መቋቋም ተስኖት እግሬ አውጭኝ ብሎ ከመፈርጠጡም ባሻገር የውጊያ ሞራሉ ክፉኛ በመዳከሙ ምክንያት በአድጎሹ ፣ አደባይ፣ሁመራና እድሪስ አካባቢ የሚገኙ የጦር አመራሮች በመሰባሰብ የመልሶ መቋቋም እንቅስቃሴ ላይ እንደተወጠሩ ታውቋል።
ነበልባል በመባል የሚታወቀው ልዩ ኮማንዶ የኢህአግ ሰራዊት በአርማጭሆ፣ ጠገዴና ወልቃይት ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት በመፈፀምና ሕዝቡን በማንቃት እንዲሁም በማስታጠቅ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ሴት ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ያሉበት በርካታ ወጣቶችን ወደ ትግሉ ጎራ እንዲቀላቀሉ አስችሏል።

ግንባሩን በጥር 18-2005 ዓ.ም የተቀላቀሉ ሴት አርበኞች የወቅቱን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያም እኛ ሴቶች አገራችን ኢትዮጵያ አይታው በማታውቅ ሁኔታ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካው መስክ አዘቅት ውስጥ እንደምትገኝ አብራርተው የእነሱ የትጥቅ ትግልን የመጨረሻ አማራጭ አድርገው የደም፣ የአጥንት፣ የጊዜ፣ የጉልበት፣ የእውቀት ብሎም የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈለ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን ለመቀላቀል ኢትዮጵያዊነት ስሜታቸውና ሕሊናቸው እንዳስገደዳቸው በመግለፅ መላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ዘር፣ ቋንቋ፣ ሐይማኖትና ፆታ ሳይለይ ከትግሉ ጎራ በመሰለፍ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ከጥፋት ሃይሉ የእብሪተኛ ቡድን የምናላቅቅበት ወቅት አሁን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን በጥር 18-2005 ዓ.ም የተቀላቀሉ ሴት አርበኞች አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር

No comments:

Post a Comment