Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Friday, January 25, 2013

ግኡሽ አበራ ከቪኦኤ የትግርኛው ፕሮግራም ጋር ያደረገው ቃለ-ምልልስ

ትርጉም በእየሩሳሌም አርአያ Interview on Monday, January 14, 2013



ጉዕሽ፥ በእኔ በኩል የነበረውን አጠር አድርጌ ልግለፅ፤ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ነኝ።


..ከተቃዋሚዎች ጋር እኛ ደጋፊዎች የተለየ ሃሳብ ነው የምንፅፈው። ያው እኔም አገሬን፡ ሕዝቤን ስለምወድና የመንግስትም ደጋፊ ስለሆንኩ ተፅፎ ያየሁትን ( የአበበ ገላው ፎቶ ያለበት እሱ ይፃፈው አይፃፈው) ግን መለስን ገድዬዋለሁ፤ ሌሎችንም እገድላለሁ፤ በተለይ ወያኔዎችን እንገድላለን» የሚሉ ፅሁፎችን ስለምመለከት ..ከዚህ በመነሳት እነሱ የሚያደርጉትን ማስፈራራት እኔም ለማስፈራራት ስል በዛ መሰረት ፅፌያለሁ።



ጥያቄ፥ ምን ብለህ ነው የፃፍከው?


ጉዕሽ፥ ያው ወያኔዎችን እንገድላለን ሲሉ፤ እኛም መልሰን እንገድላችኋለን ብዬ የመሰለኝን ፅፌላቸዋለሁ።



ጥያቄ፥ በተለይ አበበ ገላውን ጠቅሰህ ነው የፃፍከው?


ጉዕሽ፥ አዎ ለእርሱ ለአበበ ገላው ፅፌለታለሁ::

ጥያቄ፥ አንተ ከመግደልህ በፊት እኛ ቀድመን እንገድልሃለንየሚል ነገር ፅፈሃል?

ጉዕሽ፥ አዎ እርሱ ሲፅፍ ..አንተ ከመግደልህ በፊት እኛ ቀድመን እንገድልሃለን ብዬ ፅፌለታለሁ።

ጥያቄ፥ ወደ አሜሪካ ኤፍ ..አይ ምርመራ ቢሮ ሪፖርት አድርጎብህ ነበር?

ጉዕሽ፥ ሪፖርት ማድረጉን ሰምቻለሁ። ከዛም መጥተው አናግረውኛል፤ .<ይህን ብለህ፡ እንዲህ ብለህ ፅፈሃል> ብለው ጠይቀውኛል፤

ጥያቄ፥ እነማን ናቸው መጥተው ያናገሩህ?

ጉዕሽ፥ ኤፍ..አይ ናቸው መጥተው ያናገሩኝ

ጥያቄ፥ መቼ መጥተው አናገሩህ?

ጉዕሽ፥ ከሁለት ሳምንት በፊት ነው መጥተው ያናገሩኝ..በፈረንጆች ገና..

ጥያቄ፥ እሺ ቀጥል ..

ጉዕሽ፥ ጠየቁኝ፤ እኔ ደግሞ ነገርኳቸው። ለተፃፈው ፅሁፍ ነው መልስ የሰጠሁት ብዬ ነገርኳቸው። የተፃፈውን ፅሁፍ አሳዩኝ፤ እንገድላለን ብለው ለፃፉት እኛም እንገድላለን ብዬ መልሻለሁ። የፃፍኩት ለማስፈራራት እንጂ ሆነ ብዬ ያሰብኩበትናደርገዋለሁ ብዬ አይደለም። አለ አይደል እኔ በፅሁፍ (ቃል) ለማስፈራራት ያክል የመለስኩት ነው። እነርሱ ያሉት ግን አበበ ገላውን ለመግደል ከሌሎች የስርዓቱ ሰዎች ጋር ሲመክር ተያዘ፤ የተባለው ልክ አይደለም። እኔ ሁል ጊዜም በስራ ተጠምጄው የምውለው፤ ጊዜ የለኝም።

ጥያቄ፥ በማንኛውም መንገድ ከኢትዮጲያ የፀጥታ ተቋማት ጋር ምንም ግንኙነት የለህም?

ጉዕሽ፥ እኔ ከመንግስት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም። የመጣሁት በ 2008 ሲሆን አመጣጤም በዲቪ ነው። ተማሪ እያለሁ ዪኒቨርሲቲ ልገባ ስል ዲቪ ደረሰኝና ወደዚህ አገር መጣሁ። እኔ ከመንግስት ጋርም ሆነ መንግስትን ከሚመለከት ስራ ጋርንም ግንኙነት የለኝም።

ጥያቄ፥ ለመሆኑ የት አገር ነው የምትኖረው?

ጉዕሽ፥ ቦስተን ነው ያለሁት

ጥያቄ፥ ለኤፍ..አይ ስትነግራቸው እነሱ ምን አሉህ?

ጉዕሽ፥ በፅሁፍ እንዲህ ብላችሁ መመላለሳችሁ ጥሩ አይደለም አሉኝ። ግን ምንም ችግር የለብህም ብለው ነግረውኛል።"አበበ ገላውን ለመግደል ከሰዎች ጋር ሲያሴርና ሲሰልል ተገኘ’’ የሚል ነው በቪዲዮ ወጥቶ ያየሁት፤ እኔ ግን እንደዚያ አይነት ስራ አልነበረኝም።

ጥያቄ፥ ሰዎችን ማስፈራራት ጥፋት እንደሆነ ገልፀውልህ ይሆናል።.በአንተም ሆነ በእሱ ወይም በሌላው ዛቻ ማድረስ በዚህ አገር ጥፋት እንደሆነ ታውቃለህ?

ጉዕሽ፥ እንገድልሃለን ሲሉህ - እንገድላችኋለን ..ብለህ መልስ መስጠት ጥሩ እንዳልሆነ ነው የነገሩኝ። እኔም ሆነ ብዬ

የፈፀምኩት ሳይሆን፥ ባለው የአገር ስሜት እኔም አገሬን የምወድ በመሆኔ ከዛ ስሜት ተነስቼ የፃፍኩት እንጂ ሆነ ብዬ

አይደለም። አበበ ገላው ምን አይነት ሰው እንደሆነ፡ የት አገር እንደሚኖር የማውቀው ነገር የለም። እንገድላችኋለን

ለምትለው እኔም የሚመስለኝን ፅፌያለሁ እንጂ እኔ ለመግደል ያደረኩት ነገር የለኝም።

ጥያቄ፥ ኤፍ..አይ ከዛ በኋላ ተመልሰው አገኙህ?..አንድ ጊዜ ብቻ ነው ያነጋገሩህ?

ጉዕሽ፥ ቪዲዮው ከወጣ በኋላ ጠይቀውኛል፤‘’ ደህና ነህ ወይ? እንዴት ነህ?’’ ብለው ጠየቁኝ.. 

ጥያቄ፥ ለሁለተኛ ጊዜ?

ጉዕሽ፥ አዎ ለሁለተኛ ጊዜ። ቪዲዮው ከወጣ በኋላ መጥተው« ያለውን እንቅስቃሴ ተመልክተናል። ምንም ችግር ስለሌለብህ አትጨናነቅ ብለው ነው የነገሩኝ..

ጥያቄ፥ ስለዚህ ለደህንነትህ ሲሉ ነው የመጡት ማለት ነው::

ጉዕሽ፥...ስለእኔ ሁኔታ ከጠየቁኝ በኋላ በተመሳሳይ ስለእኔ የሚፃፉትንና የሚደረጉትን ዝም ብለህ መከታተል አለብህ ብለው ነው የነገሩኝ

ጥያቄ፥ መጀመሪያ ምን ያክል ሰዓት አነጋገሩህ?

ጉዕሽ፥15 ደቂቃ ገደማ ነው ያነጋገሩኝ፤ ሲመጡ ስራዬ ላይ ነበርኩ።

ጥያቄ፥ የመዘገቡት ነገር ነበር ..

ጉዕሽ፥ አዎ፤ እኔ በበኩሌ በቪዲዮ ላይ ስለወጣው የስም ማጥፋት ማለት በመንግስት የተላከ ነው፤በአሳይለም የሚኖር ሰላይ ነው ’’ ስለተባለው ጠይቄያቸዋለሁ። ሌላው ከመንግስት ጋር ግንኙነት አለው ስለተባለው ነግሬያቸዋለሁ። እኔ በአሳይለም አይደለም የመጣሁት። በአሳይለም አይደለም የምኖረው

ጥያቄ፥ እሺ በመጨረሻ በምን መደምደሚያ ተሰናበታችሁ? ነፃ መሆንህን አረጋገጡልህ?..ኤፍ..አይ. ምን ዋስትና ሰጥተው አሰናበቱህ?

ጉዕሽ፥ ምንም መጨናነቅ የለብህም፤ እንዲህ አይነት ፅሁፍ የለብህም.. ብለው ነው የነገሩኝ። ኤኒቲንግ ሃፕን

..የሚያስፈራራህ ሰው ካለ ያው ስለቤተሰቤ ሁኔታና ከመንግስት ጋር ግንኙነት ነበረህ ወይ ብለው ጠይቀውኛል፤

ወላጆቼ ምን ይሰሩ እንደነበርና ወላጆቼም ከመንግስት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው የራሳቸውን ንግድ እንደሚሰሩ፡ እኔም ተማሪ እንደነበርኩ፤ ከመንግስት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለኝ ነገር ግን እንደ አገር ልጅነቴ የመንግስት ደጋፊ..ህዝቤንም እወዳለሁ፤ እደግፋለሁ ብያለሁ።

ጥያቄ፥ ከዚህ ሁኔታ በኋላ ከወዳጆችህ እና ተቃዋሚ ከሚባሉ ምን አይነት ምላሽ እያገኘህ ነው?

ጉዕሽ፥ አይዞህ የሚል ሞራል ነው ጓደኞቼና ሌሎች በውጭ አገራት የሚኖሩ በስልክ ጭምር እየደወሉ“አይዞህ በተፈጠረው ሁኔታ መናደድ የለብህም፤ ሌላም ነገር ካለ ልንተባበርህ ዝግጁ ነን” ብለው ነው የነገሩኝ።

መጨረሻ የጋዜጠኛው ማጠቃለያ፥

የኤፍ..አይ ምርመራ ቢሮ በሰጠው ምላሽ የግድያ ሙከራ ነበረ ለማለት የሚያስችል ማስረጃ አላገኘንም፤ ክስም አልመሰረትንም” ብሏል።

አበበ ገላው በቢጫ የተሰመረበትን አባባል ተዛብቶ ካልቀረበ በቀር ካለው እውነታ አንጻር በምርመራ ተይዞ በሚገኝ ጉዳይ ላይ ማንም ሊናገረው የሚችል አይመስለኝም፣ ሆኖም ጉዳዩን እናጣራለን ብሏል። ከዚህም አክሎ ከግኡሽ አበራ ጋር ፈጽሞ ምንም አይነት ግንኙነትም ሆነ ትውውቅ ኖሮን አያውቅም ብሏል::

በግኡሽ ላይ ምንም አይነት ጥቆማም ሆነ ክስ አቅርቤ አላውቅም፣ የFBIን ትኩረት የሳበውም በራሱ ህገወጥ እንቅስቃሴ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል። በዘሩ ምክንያት የደረሰበት ችግር እንደሆነ በርሱም ሆነ በሌሎች የተነገረው አባባል ፈስሞ ከእውነት የራቀ አጸያፊ የህወሃቶች ትሮፓጋንዳ መሆኑን አስምሮበታል። በግለሰቡም ሆነ በአንዳንድ የህወሃት ሰዎች እኔን አስመልክቶ እየተናፈሰ ያለው የሀሰት እና የጥላቻ ቅስቀሳ ከነመረጃው ለሚመለከታቸው የህግ አካላት አቀርባለሁ በማለት አስግንዝቦ ተመሳሳይ ህገወጥ ጥረቶች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባቸዋል በማለት ተናግሯል።

Source Addisvoice

http://tigrigna.voanews.com/content/tig-abebegelaw/

1583711.html?

No comments:

Post a Comment