አለቃ ገብረ ዮሐንስ አባዲ ይባላሉ፡፡ ዕድሜያቸው 39 ሲሆን፣ የስድስት ልጆች አባት ናቸው፡፡ በትግራይ ክልል ደጉዓ ተምቤን ወረዳ አረጌ በሚባል ቀበሌ አካባቢ ይኖራሉ፡፡
የሚተዳደሩት በግብርና በመሆኑ ሞዴል ገበሬ (ሞዴል ሐረ ስታይ) ናቸው፡፡ ገበሬ ብቻም አይደሉም፡፡ ጥቂት ለማይባሉ ዓመታት የቀበሌው የወጣቶች ማኅበር ሊቀመንበር ሆነው ሲሠሩ ነበር፡፡ ‹‹ዓዲ ሐርሐር›› በመባል በሚታወቀው 25 አባላት ባሉት ‹‹የልማት ቡድን›› ታቅፈውም ሠርተዋል፡፡ አምስት አምስት በመሆን በአምስት አነስተኛ ቡድኖችም የተከፋፈለ ነው፡፡ እያንዳንዱን ቡድን አንድ የሕወሓት አባል (ካድሬ) ይመራዋል፡፡
የልማት ወይስ የፖለቲካ ቡድኖች?
አለቃ ገብረ ዮሐንስ ያሉበት ቡድንን ጨምሮ ‹‹የልማት ቡድኑ›› ዓላማ ገበሬዎች ማዳበርያ እንዲጠቀሙ ማድረግ፣ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል፣ አዳዲስ ምርጥ ዘሮችንና አዳዲስ የእርሻ ቴክኖሎጂን ማስተዋወቅ፣ በመስኖና በሌሎች የእርሻ ሥራዎች ገበሬዎች እርስ በርሳቸው ተሞክሮአቸውን እንደለዋወጡ ማገዝ ነው፡፡ እባከዎን ሙሉውን ላማንበብ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ
No comments:
Post a Comment