Sunday, January 13, 2013
የሳምንቱ የፍትህ ራዲዬ ጠቃሚ ዜና
የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በድብቅ ያደረጉት ስብሰባ ተጋለጠ
ከፍትህ ራዲዬ የተወሰደ
የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የብሔራዊ ደህንነት ሃላፊዎች እና የፖሊስ አመራሮች በድብቅ ካሳንቺስ አካባቢ ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ ያደረጉት ስብሰባ ተጋለጠ፡፡በስብሰባው ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደምቅሳ፣የብሔራዊ ደህንነት እና መረጃ መረብ ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ጌታቸው ፣የአዲስ አበባ ፍትህ እና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ፀጋዬ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በሙስሊሙ ላይ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ ተወያይተዋል፡፡ መድረኩን ሲመሩ ከነበሩት የመንግስት ባለስልጣናት በኩል የሙስሊሙ ተቃውሞ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ይገኛል፡፡ ከአዲስ አበባ ወቶ በክልል ከተሞች እየተስፋፋ ሲሆን ከዛም አልፎ በአለም ደረጃ ተሰሚነትን እያገኘ በመሆኑ ከወዲሁ መፍትሄ ካልተበጀለት የፓርቲያችን ህልውና አደጋ ውስጥ ይወድቃል በማለት ተናግረዋል፡፡
በየቦታው ተቃውሞውን የሚያሰማው ህዝብ ከልቡ ፈልጎ ሳይሆን ከአሜሪካና ከአውሮፓ ተቃውሞ እንዲያካሂዱ ገንዘብ ስለሚላክላቸው እና ለእያንዳንዱ ሰው ስለሚከፈለው ነው ብለዋል፡፡ ተቃውሞ የሚካሄደው ከአውሮፓ እና ከአሜሪካ በሚላክ ገንዘብ ስለመሆኑ የደህንነት ክፍላችን በሚገባ አረጋግጦል ብለዋል፡፡ቀጥለውም አዲስ የተመረጠው የአዲስ አበባ መጅሊስ ምን እየሰራ ነው በማለት ተቃውሞውን ለማስቆም በየመስጂዱ ትምህርት መስጠት አለመቻሉን ክፉኛ ኮንነዋል፡፡ በኛ በኩል ጥሩ ይሰራልናል የምንለው የ አንዋር መስጂድ ኢማም ሀጂ ጠሃ ነው፡፡ አሱም ለመስራት ድፍረቱ ቢኖረውም ከህዘቡ ጋር ባለው የሻከረ ግንኙነት ምክንያት መስራት አልቻለም ብለዋል፡፡ ለተስብሳቢዎቹም በየቦታው ለወላጆች ልጆቻቸውን የተቃወሞ ቦታ እንዳይገኙ እንዲይዙ አጥብቀው እንዲያስጠነቅቁ እና እንዲያስፈራሩ ትዛዝ ተሰዋል፡፡
ከተሰብሳቢዎቹም መሃል ፣የአዲስ አበባ ፍትህ እና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ፀጋዬ በሰጡት አስተያየት ባሁኑ ወቅት እጅግ በጣም ያሳሰባቸው ጉዳይ የራሳቸው ካድሬዎች ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ መንግስት እርምጃ ሲወስድ ካድሬው ወደኛ በመምጣት የታሰረው እኮ የኔ ቤተሰብ ነው በማለት እንዲፈቱ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፤ በካድሬው መካከል ሚስጥር መጠበቅ የሚባል ነገር ፈፅሞ የጠፋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በመሃከላችን ተሰብስበው ከሚገኙት መካከል አሁንም ሃሳባቸው ሌላ ቦታ ያሉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡እዚህ የተሰበሰብነውን ስብሰባ ስንወጣ ፌስቡክ ላይ ይለቁታል፡፡ ዝርዝሩን ደግሞ አንዲት ሬዲዬ አለቻቸው በዛ ሬዲዬ ለህዝቡ ይለቁታል በማለት መማረራቸውን ገልፀዋል፡፤ አሁን አሁን ግን ባለቤቴን እና ልጆቼንም ማመን ተስኖኛል በማለት ሚስጥራቸው እየወጣ መሆኑ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዝርዝሩን ከፍትህ ሬዲዬ ያዳምጡ
http://bit.ly/UInN2B

No comments:
Post a Comment