Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Thursday, February 14, 2013

በስዊድን 136 000 ክሮነር ለኢሳት ተሰበሰበ

*የገንዘቡ መጠን በስዊድን ከክብረወሰን ተመዝግቧል

*ሙስሊሙና ክርስቲያኑ አንድነቱን ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳይቷል

Artist and activist Tamagne Beyene in SwedenEthiopia Zare (ሰኞ የካቲት 4 ቀን 2005 ዓ.ም. February 11, 2013)፦ ቅዳሜ የካቲት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም በተካሄደው የኢሳት (የኢትዮጵያ ሳተላይ ቴሌቭዥን) የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 136 ሺህ የስዊድን ክሮነር የተሰበሰበ ሲሆን፤ በዚህ ዝግጅት ላይ ሙስሊም ኢትዮጵያውን ከመቼውም ጊዜ በላይ ተሳትፎ ያደረጉበት መሆኑ ታውቋል።
አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በተገኘበት በዚሁ ዝግጅት ላይ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን፣ ወጣት ኤርትራውያን እንዲሁም ስዊድናውያን ተገኝተዋል። ዝግጅቱ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ይጀምራ የተባለ ቢሆንም፤ ከሁለት ሰዓት በላይ አርፍዶ ተጀምሮ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ተጠናቅቋል። በስዊድን ከተደረጉ ዝግጅቶች ውስጥ ይኸኛው ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ማኅበረሰብ አንድነቱን ከመቼውም ጊዜ በላይ ያሳየበት መሆኑን የኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍል ለመረዳት ችሏል።

በዝግጅቱ ላይ የስዊድን ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርላማ አባልና የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ተወካይ የሆኑት ክብርት ካሪና ሄግ እንዲሁም በኢትዮጵያ ታስረው ከነበሩት የስዊድን ጋዜጠኞች አንዱ ማርቲን ሺቤ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
Ethiopian Muslims and Christians in Sweden
ዝግጅቱን በንግግር እንዲከፍቱ የተጋበዙት የክርስትና እና የእስልምና ኃይማኖት አባቶች ነበሩ። እነርሱም ቀሲስ ፍሰኀ ከክርስትናው እና አቶ ሶፊያን ከእስልምና ኃይማኖት ሲሆኑ፣ ሁለቱም አባቶች ጎን ለጎን በመቆም ባደረጉት ንግግር የታዳሚዎችን ቀልብ የሳበ ንግግር አድርገዋል። የኃይማኖት አባቶቹ የኢትዮጵያን ታሪክ ከኃይማኖቶቻቸውን ጋር በማገናኘት በኢትዮጵያ ውስጥ የሁለቱ ኃይማኖቶች ምዕመናን በኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 1434 ዓመታት ተከባብረው በሠላምና በፍቅር መኖራቸውን ገልጸዋል። አክለውም ኢሳትን በሁሉም አቅጣጫ በሞራል፣ በማቴሪያል፣ በገንዘብ፣ በሙያ፣ … የመደገፍ የሁላችንም የሕሊና ግዴታ ነው ሲሉ ተናግረዋል። እባከወት በሙሉ ለማንበብ እዚህ ላይ በከርሰሩ ክሊክ ያድርጉት

No comments:

Post a Comment