ከትዕዝብ አድማሱ
የሐራካት ፊልም ድራማ ህዝቡን ያስተባብሯል እንጂ አይለያየንም
ትግሉን ያቀጣጥለዋል እንጂ አንገት አያስደፋንም
ሰሞኑን ሁላችንም እንዳየነው ወጣት ሙስሊም ወንድሞቻችን ሕገ መንግስቱ የሰጠንን የእምነት ነፃነታችን ይከበር በማለት በሕጋዊ አገባብ መልስ እንዲሰጣቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው በሓሰት ላይ የተመሰረተ ሓራካት የሚል የፊልም ድራማ በኢትዮጵያ ተለቪዥን ላይ ሲታይ መሰንበቱ ይታወቃል። የፊልሙ ይዘት በሶስት ነጥቦች ከፍሎ ማየት ይቻላል።1. ፊልሙ ምን አዲስ ነገረ አለው?
2. የፊልሙ አላማ ምንድን ነው?
3. ፊልሙስ እንዳሰቡት ግቡን መቷልን? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ቀጥለን እንመልከት።
1. የሙስሊም ሐራካት የፊልም ድራማ ምን አዲስ ነገር አለው?
ፊልሙ አዲስ ነገር የለውም። እንደዚህ ዓይነት በውሸት ላይ የተመሰረተ ማደናገሪያ ድራማ ማቅረብ የተለመደ፣ በተለይም ህወሓቶች ከተፈጠሩበት ቀን ጀምረው እስካሁን ድረስ በተለይም ምርጫ ሲቃራብ፣ የሚፈልጉትንና የሚጠረጡሩትን ሰው በእጅ አዙር ለመምታት፣ የህዝቡን ቀልብ ለመቀየር፣ የፓለቲካ ተቃዋሚዎችን ለማስደንገጥና ወኔ ለመስለብ ሲሉ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሙት የስነ ልቦና ጦርነትና ዘመቻ ነው። ለምሳሌ ወደ ዛሬው ድራማ ከመሄዳችን በፊት ህወሓቶች ስልጣን ከያዙ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከፈፀሙት አሰቃቂ ድርጊቶች ውስጥ ቆንጥረን የሚከተሉትን እንመልከት፡-
ተቃውሞ ከህዝቡም ሆነ ከፓለቲካ ድርጅቶች እየበረታ ሲሄድ ከሚጠቀሙት ዘዴ አንዱ ድሮ የተረሳና ከአሁኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ ምንም ተያያዥነት የሌለው ደኩመንት ከማሕደር እየመረጡ ከዘውዳዊ ስርዓት፣ ከደርግ ጭቆና፣ ከሻዕቢያ ወራር፣ ከሽብርተኝነትና ከጦርነት ጋር የተያያዘ ፊልም አቀነባብረው ለዓይን እስከሚሰለች ድረስ ያቀርባሉ። መልእክቱም ቂማችን አልረሳንም ተጠንቀቁ ለማለት ነው። በሙሉ ለማንበ የሚከተለውን ማጣቅሻ ይጫኑት http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6029
No comments:
Post a Comment