Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Tuesday, February 5, 2013

በአክሱም ዩኒቨርስቲ በተነሳ ግጭት በርካታ ተማሪዎች ተጎዱ

 ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም


ኢሳት ዜና:- በዩኒቨርስቲው በተማሪዎች እና በአስተዳዳሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች የተፈነከቱ ሲሆን የዩኒቨርስቲው መኪናዎች ተማሪዎች ባወረዱት የድንጋይ ናዳ ተሰባብረዋል። የመማሪያ ክፍሎች መስታውቶች እና አንዳንድ በግቢው ውስጥ የሚታዮ እቃዎችም ተሰባብረዋል።

ተቃውሞው ባለፈው ቅዳሜ ጥር 25 የተነሳው ሁለተኛ ግጭት በምግብ መበከል ሲሆን ዩኒቨርስቲው ከትምህርት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ስራ ብዙ ጊዜ በማዋሉ እና የአስተዳደር አባላቱ ሙስና ላይ በመዘፈቃቸው ተማሪዎች የዩኒቨርስቲው ሁለት ምክትል ዲኖች ይውረዱልን ሲሉ ምሬታቸውን አሰምተዋል።

በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ ግጭቱ ሲቀሰቀስ የአካባቢው ሚሊሺያዎች ትኩስ እያሰሙ ወደ ግቢው ቢገቡም መብረድ ባለመቻሉ እና ይበልጥ በመቀታጠሉ የክልሉ ፖሊስ አስለቃሽ ጪስ በመተቀም ግቢውን የተቆጣጠሩት ሲሆን ምሽቱን በሚኒባስ ፌደራል ፖሊስ ገብቶ ግቢውን ተቆጣጥሮ 10 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር አውሎአል፡
የዩኒቨርስቲው አስተዳደር በትናንትናው እለት ተማሪዎችን ለማረጋጋት እንደራደር ቢልም ተማሪዎች ግን መጀመሪያ የታሰሩ ተማሪዎችን ፍቱ ቀጥሉና ሁለቱን ምክትል ዲኖች ከሀላፊነት ይውረዱና ይጠየቁልን ብለዋል።
ተማሪዎች ዛሬም ትምህርት አለመጀመራቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል።

No comments:

Post a Comment