እነሆ ለብዙ
አመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ አምባገነን ገዢዎች እየተፈራረቁበት ሰባዊ መብቱ እየተረገጠ የእምነት ነጻነቱ ተገፎ
የመሰብስብ፣ የመፃፍ፣ የመናገር፣ የመደራጀት መብቱ ታፍኖ ለፋሺስትና ለወያኔ ሲገብር እየኖረ ይገኛል። ከሁሉም ጊዜ
በከፋ ሁኔታ ደሞ አሁን ባለንበት ዘመን ኢትዮጵያ ሐገራችን በወያኔ የሐገር ማጥፋት ህልም የተነሳ ሰንደቅ
አለማችንን፣ አንድነታችን፣ ታሪካዊ ቅርሳችንን፣ ውድ መሬታችንን፣ ሀይማኖታችንን ከመድፈር አልፎ እያፈረሰና በከፍተኛ
ፍጥነት በሐገር ውስጥ በበቀሉ ከሀዲዎችና በውጭ ጠላቶቻችን ርብርብ እየወደመ ይገኛል።
ዛሬም ጠባብነትና
ግለኝነት ነግሶ ማመን በሚያቅት ግዝፈትና ፍጥነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመከፋፈልና ለመበታተን ሀገራችንን በደም
ውቅያኖስ ለመሸፈን የሚደረገው ሴራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የወያኔ ነፍሰ ገዳዮች በተቃዋሚው ጎራ ሰርገው በመግባት
አልፎም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ተብዬዎችን ጨምር በመምራት ለወያኔ ድጋፍና ሽፋን ከመስጠት አልፈው የህዝቡን
ትግል አቅጣጫ በማሳት የወያኔን እድሜ አያራዘሙ ይገኛሉ። ብዙዎች የፖለቲካ መሪዎችም ከሀገር ጥቅም ይልቅ የግል
ፍላጎታቸውን በማስቀደም በእኔ እበልጥ በእኔ እበልጥ በሽታ ተለክፈው የጋራ ጠላት የሆነውን ወያኔን በተጠናከረና በተባበረ የሕዝብ ትግል ከስልጣን ለማውረድ ለሚደረገው ጥረት እንቅፋት ሆነዋል።
ይህንን ክፍተት በመጠቀም ከመቃብሩ አፋፍ ላይ ቆሞ በጣረ ሞት የሚወራጨው ወያኔ ተገርስሶ ከመውደቁ በፊት በቀረችው
የመጨረሻ ትንፋሽ እነሆ የማደናቆርያና የማደንዘዣ እኩይ ተግባሩን አጠናክሮ ገንዘብ ሊገዛው በሚችለው የሀሰት
ፕሮፕጋንዳ ሕዝባችንን ለመከፋፈልና እርስ በእርስ ለማጫረስ ያዘጋጀው የመጀመርያ ትእይንት ለአየር በቅቷል።
ሁለተኛውን ክፍል ደግሞ በክርሥትና ሃይሞኖት ላይ በማተኮር ለሃይማኖታቸው፣ ለህዝባቸውና ለሐገራቸው እንጂ ለወያኔ
የበግ ለምድ ለባሽ የታጠቁ ካድሬዎች አልገዛም ያሉትን፣ ለገዳማችን ለኦርቶዶክሥ እምነታችንና ለታሪካዊ ቅርሳችን ዘብ
የቆሙትን፣ ፍቅርን፣ አንድነትንና ሰላምን የሚሰብኩትን፣ ግፍና ሰቆቃን አንባርክም ያሉትን፣ እውነተኛ የኦቶዶክሥ
እምነት አባቶች ጥላሸት ለመቀባት እየተፍጨረጨረ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቂት ባለጊዜዎች የሐገሪቱን ሀብት
ተቧድነው እየዘረፉ ያላግባብ እየተንደላቀቁ በጠኔ አንጀቱ የታጠፈውን ምስኪን በቁንጣን ልትሞት ነው ቢሉት፣ ግፍና
ሰቆቃ በዝቶ ሰው ሞቱን እየመረጠ እራሱን በእሳት ሲያቃጥል እያዩ በምፀት ፌዝ ደስታህ ገደብ የለውም ቢሉት፣ በውሃና
በመብራት እጥረት ሕይወት ሲኦል ሆኖበት ሳለ የራሳቸውን ምቾት እያሰሉ ኑሮሕ ከአስር በመቶ በላይ አድጏል ቢሉት፣
በሰላማዊ መንገድ መብቴን ባለ በጥይት እየቆሉት፣ ገድለው እሬሳውን መሬት ለመሬት እየጎተቱት፣ እስርቤቶቹ ተጣበው
በገዛ ሐገሩ ይቁም እስረኛ አድርገው እያሰቃዩት፣ ነፃነት ገደብ የለውም ብለው ቢያዜሙለት ከአንጀቱ ጠብ የማይል ባዶ
የተስፋ ዳቦ ሊያስገምጡት ቢቃጡ ከንቱ ድካም እንጂ እውነታው አይለወጥም።
ኢሕአፓ ወክንድም እደ ኦርቶዶክስ
እና እስልምና እምነት አባት መሪዎች የሁለቱም እምነት አማኞች ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ለእምነት ነፃነታቸው
የሚያደርጉትን ትግል አቀናጅተው ወደከፍተኛ ደረጃ እንዲያሸጋግሩት ጥሪ እያደርገ የሁላችንም ጠላት የሆነው ወያኔ
እንዲወገድ እንዲሁም ሀገራችን እና ሕዝባችን ነፃ እንዲወጣ እስከመሰዋትነት ያለውን ዝግጁነት በድጋሚ ያረጋግጣል።
ፀረ ወያኔው ሕዝባዊ ትግላችን ይፉፉም!!
እናቸንፋለን!!!
እነሆ ለብዙ አመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ አምባገነን ገዢዎች እየተፈራረቁበት ሰባዊ መብቱ እየተረገጠ የእምነት ነጻነቱ ተገፎ የመሰብስብ፣ የመፃፍ፣ የመናገር፣ የመደራጀት መብቱ ታፍኖ ለፋሺስትና ለወያኔ ሲገብር እየኖረ ይገኛል። ከሁሉም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ደሞ አሁን ባለንበት ዘመን ኢትዮጵያ ሐገራችን በወያኔ የሐገር ማጥፋት ህልም የተነሳ ሰንደቅ አለማችንን፣ አንድነታችን፣ ታሪካዊ ቅርሳችንን፣ ውድ መሬታችንን፣ ሀይማኖታችንን ከመድፈር አልፎ እያፈረሰና በከፍተኛ ፍጥነት በሐገር ውስጥ በበቀሉ ከሀዲዎችና በውጭ ጠላቶቻችን ርብርብ እየወደመ ይገኛል።
ዛሬም ጠባብነትና ግለኝነት ነግሶ ማመን በሚያቅት ግዝፈትና ፍጥነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመከፋፈልና ለመበታተን ሀገራችንን በደም ውቅያኖስ ለመሸፈን የሚደረገው ሴራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የወያኔ ነፍሰ ገዳዮች በተቃዋሚው ጎራ ሰርገው በመግባት አልፎም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ተብዬዎችን ጨምር በመምራት ለወያኔ ድጋፍና ሽፋን ከመስጠት አልፈው የህዝቡን ትግል አቅጣጫ በማሳት የወያኔን እድሜ አያራዘሙ ይገኛሉ። ብዙዎች የፖለቲካ መሪዎችም ከሀገር ጥቅም ይልቅ የግል ፍላጎታቸውን በማስቀደም በእኔ እበልጥ በእኔ እበልጥ በሽታ ተለክፈው የጋራ ጠላት የሆነውን ወያኔን በተጠናከረና በተባበረ የሕዝብ ትግል ከስልጣን ለማውረድ ለሚደረገው ጥረት እንቅፋት ሆነዋል።
ይህንን ክፍተት በመጠቀም ከመቃብሩ አፋፍ ላይ ቆሞ በጣረ ሞት የሚወራጨው ወያኔ ተገርስሶ ከመውደቁ በፊት በቀረችው የመጨረሻ ትንፋሽ እነሆ የማደናቆርያና የማደንዘዣ እኩይ ተግባሩን አጠናክሮ ገንዘብ ሊገዛው በሚችለው የሀሰት ፕሮፕጋንዳ ሕዝባችንን ለመከፋፈልና እርስ በእርስ ለማጫረስ ያዘጋጀው የመጀመርያ ትእይንት ለአየር በቅቷል። ሁለተኛውን ክፍል ደግሞ በክርሥትና ሃይሞኖት ላይ በማተኮር ለሃይማኖታቸው፣ ለህዝባቸውና ለሐገራቸው እንጂ ለወያኔ የበግ ለምድ ለባሽ የታጠቁ ካድሬዎች አልገዛም ያሉትን፣ ለገዳማችን ለኦርቶዶክሥ እምነታችንና ለታሪካዊ ቅርሳችን ዘብ የቆሙትን፣ ፍቅርን፣ አንድነትንና ሰላምን የሚሰብኩትን፣ ግፍና ሰቆቃን አንባርክም ያሉትን፣ እውነተኛ የኦቶዶክሥ እምነት አባቶች ጥላሸት ለመቀባት እየተፍጨረጨረ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቂት ባለጊዜዎች የሐገሪቱን ሀብት ተቧድነው እየዘረፉ ያላግባብ እየተንደላቀቁ በጠኔ አንጀቱ የታጠፈውን ምስኪን በቁንጣን ልትሞት ነው ቢሉት፣ ግፍና ሰቆቃ በዝቶ ሰው ሞቱን እየመረጠ እራሱን በእሳት ሲያቃጥል እያዩ በምፀት ፌዝ ደስታህ ገደብ የለውም ቢሉት፣ በውሃና በመብራት እጥረት ሕይወት ሲኦል ሆኖበት ሳለ የራሳቸውን ምቾት እያሰሉ ኑሮሕ ከአስር በመቶ በላይ አድጏል ቢሉት፣ በሰላማዊ መንገድ መብቴን ባለ በጥይት እየቆሉት፣ ገድለው እሬሳውን መሬት ለመሬት እየጎተቱት፣ እስርቤቶቹ ተጣበው በገዛ ሐገሩ ይቁም እስረኛ አድርገው እያሰቃዩት፣ ነፃነት ገደብ የለውም ብለው ቢያዜሙለት ከአንጀቱ ጠብ የማይል ባዶ የተስፋ ዳቦ ሊያስገምጡት ቢቃጡ ከንቱ ድካም እንጂ እውነታው አይለወጥም።
ኢሕአፓ ወክንድም እደ ኦርቶዶክስ እና እስልምና እምነት አባት መሪዎች የሁለቱም እምነት አማኞች ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ለእምነት ነፃነታቸው የሚያደርጉትን ትግል አቀናጅተው ወደከፍተኛ ደረጃ እንዲያሸጋግሩት ጥሪ እያደርገ የሁላችንም ጠላት የሆነው ወያኔ እንዲወገድ እንዲሁም ሀገራችን እና ሕዝባችን ነፃ እንዲወጣ እስከመሰዋትነት ያለውን ዝግጁነት በድጋሚ ያረጋግጣል።
ፀረ ወያኔው ሕዝባዊ ትግላችን ይፉፉም!!
እናቸንፋለን!!!
No comments:
Post a Comment