Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Sunday, July 28, 2013

ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የተቃዉሞ ሠልፍ

የተቃዉሞ ሠልፉና የሥብሰባዉ አስተባባሪዎች እንደገለፁት ዩናይትድ ስቴትስ፥ ካናዳ፥ አዉስትሬሊያ በተለያዩ የአዉሮጳና የመካካለኛዉ ምሥራቅ ከተሞች አደባባይ የወጣዉ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የኢትዮጵያ መንግሥት ሐማኖታዊ ነፃነትን እና ሠብአዊ መብትን እንዲያከብር፥ ጠይቋል በመላዉ ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ባደረጉት የአደባባይ ሠልፍና ስብሰባ በሐይማኖታዊ ጉዳያችን ጣልቃ ገባ ያሉትን የኢትዮጵያ መንግሥትን አወገዙ። የተቃዉሞ ሠልፉና የሥብሰባዉ አስተባባሪዎች እንደገለፁት ዩናይትድ ስቴትስ፥ ካናዳ፥ አዉስትሬሊያ በተለያዩ የአዉሮጳና የመካካለኛዉ ምሥራቅ ከተሞች አደባባይ የወጣዉ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የኢትዮጵያ መንግሥት ሐማኖታዊ ነፃነትን እና ሠብአዊ መብትን እንዲያከብር፥ ጠይቋል።የሙስሊም መሪዎችን ማሰሩን እና የእምነት ተቋማትና ትምሕርት ቤቶችን ወርሷል በማለትም አዉግዘዋል። የየሐገራቱ መንግሥታትም በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።እዚያዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በየሳምንቱ አርብ በየመስጊዱ የሚደረገዉ ተቃዉሞ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ዩናይትድ ስቴትሱን የተቃዉሞ ሠልፍ በተመለከተ የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ። ነጋሽ መሐመድ አበበ ፈለቀ አርያም ተክሌ Audios and videos on the topic የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የተቃዉሞ ሠልፍ ቀን 26.07.2013 ያጋሩ ይላኩ ፌስቡክ ትዊተር ጉግል ተጨማሪ አስተያየትዎ: ይጻፉልን! ያትሙ ገፁን ያትሙ Permalink http://dw.de/p/19Eta

No comments:

Post a Comment