Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Sunday, December 1, 2013

በሳዉዲ የኢትዮጵያዉያን ችግርና መፍትሄዉ

ኢትዮጵያ በሳውዲ ካለ ይኖሩ የነበሩ ከ50,000 የሚበልጡ ዜጎችዋን ወደ ሀገራቸው መመለስዋን በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ ማስታወቁ ይታወቃል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ችግር ያጋጠማቸውን ዜጎቹን የመመለሱን ተግባር ሲጀምር ቁጥራቸው 10,000 ይሆናል ብሎ ገምቶ ነበር።
ይሁንና፣ አሁንም በሳዉዲ ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ቁጥራቸው በውል እንደማይታወቅ እና፤ ምናልባትም ቁጥሩ ከፍ ሊል እንደሚችል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በዚሁ በያዝነዉ ሳምንት ለዶይቸ ቬለ መግለፃቸዉ ይታወሳል። በሳዉዲ አረብያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በፀጥታ ኃይላት ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰባቸዉ እና አሁንም በዚሁ ችግር ዉስጥ ያሉ ዜጎች ጥቂት እንዳልሆኑም እየተነገረ ነዉ። የዕለቱ የእንወያይ ዝግጅት በሳዉዲ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንን ላይ ስለደረሰዉ ችግር አጠቃላይ ገጽታ እና በወቅቱ ዜጎችን ለመርዳት እየተደረገ ስላለዉ እንቅስቃሴ ባልደረባዪ ጀፈር አሊ፤ ተወያዩችን ይዞ ሐሳብ አሰባስቦአል።
ጀፈር አሊ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

No comments:

Post a Comment