Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Tuesday, May 21, 2013

በኖርዌይ ኦስሎና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቅዳሜ በ18.05.13 ህዝባዊ ውይይት አደረጉ።

ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ውይይቱ በሀገራችን በግፍ ለተገደሉ፤ በእስር ለሚንገላቱና ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ለሚሰቃዩና ለተሰደዱ ወገኖች የህሊና ፀሎት በማድረግ ተጀምሯል። በርካታ ታዳሚዎችም ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ በመደገፍ ጥቁር ልብስ ለብሰው ተገኝተዋል። ውይይቱ የተጠራው በኖርዌይ ለወገን ደራሽ ግብረ ሀይል ሲሆን. በውጪ ሀገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ  ፖለቲካ ውስጥ ስለሚጫወተው ሚናና በሀገር ቤት በሰማያዊ ፓርቲ ስለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ፣. ሰላማዊና ሌሎች የትግል ስልቶች በኢትዮጵያ እና ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ፣  ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመገናኛ ብዙሀን፤ ከሰብአዊና ከዲሞክራሲ መብቶች አንጻር ፣ ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታና በሀገር ቤት ስለታቀደው የሰማያዊ ፓርቲ ተቃውሞ ሰልፍ ፣  የሀይማኖት ነጻነት በኢትዮጵያና ሰማያያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ  የሚሉት ይገኙበታል።

በነዚህ ወቅታዊና አንገብጋቢ ርዕሶች ላይ ለታዳሚዎች የመወያያ ሃሳቦችንና ገለጻዎችን ያቀረቡት በቅደም ተከተል አቶ አርጋው ያቆብ፤ አቶ ዳንኤል አበበ፤ አቶ ዳባ ጉተማ፤ አቶ ዳሂሎን ያሲን እንዲሁም አቶ ሙሀመድ ሲራጅ ሲሆኑ ዝግጅቱንና ውይይቱን የመሩት ደግሞ አቶ ዳዊት መኮንን ናቸው። በውጪ ሀገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና ሊጫወት እንደሚችል አቶ አርጋው በዝርዝ አቅርበዋል። በሚዲያና በቴክኖሎጂ በመደገፍ አገር ውስጥና ውጪ ካሉ ተቃዋሚ ሀይሎች ጋር የመረጃ ልውውጦችንና ቅስቀሳዎችን በማድረግ፤ ለአለም አቀፍ ድርጅቶች አቤቱታን በማቅረብ፤ ሰላማዊ ሰልፎችን በማድረግ፤ በመዋጮ በቁሳቁስና በሞራል ተቃዋሚ ሀይሎችን በመደገፍ፤ ገዢው አካል አለም አቀፋዊ ድጋፍ እንዳያገኝ በማድረግ፤ በሲቪክ ማህበራት በመደራጀት  ዲያስፖራው በኢትዮጵያ ለሚደረገው የዲሞክራሲና የነፃነት ትግል ጉልህና ትልቅ ሚና ሊጫወት እንደሚችል አስረድተዋል ሲል አበበ ደመቀ ከኖርዌይ ዘግቧል።
ለተጨማሪ መርጃ በኢሳት ቴሌቪዝዮን የተላለፈውን ከሌሎች የእለቱ ዜናዎችን ጭምር ይገንዘቡ፡ 


No comments:

Post a Comment