Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Sunday, November 25, 2012

የሙት ቃል ኑዛዜ እና የኢፈርት እልህ


እመት ጋለሞታ የሙስና እማማ፡
አዲስ ጎጆ ወጪ ዙፋን አገግማ፡
ብቅ አለች በመስኮት አዜብ ተሰይማ፡
የኢፈርት እንጀራ እናት ስታቦካ ከርማ፡
ሊጥ እየጋገረች ጎጥ ምጣድ ከስማ፡
በአገር እያሰፋች ጠባብ ሙግድ ገጥማ፡
እንጀራ አሳረረች አምባሻ አፈርጥማ፡
ህዝብ ሆዱ እንዲቆርጥ ንግርቱን ሲሰማ፡
በእልፍኝ በአዳራሹ ንፉጓ ተሹማ፤
የደላት ሰተቶ ‘ለባላገር ጠቅማ’፤
የከዳች እርስቷን ሺህ ሲራብ ሲጠማ።
የሟቹን ኑዟዜ ወራሹ እንዲሰማ፡
ቀርባ በቴሌቪዥን ዋልታ ሳታቅማማ፤
የሚስጢር ስንክሳር ዶሴውን ጠቁማ፡
መለስ የሸረቡት ‘ልማት- አኬልዳማ’፡
ያ! ታላቁ ‘ራዕይ’ የጎጠኞች አድማ፡
በዘር ያስደቆነ ቀበሌ ባድማ፤
ጎጥ የቤት ስራቸው በእልህ የሚያስማማ፡
የወያኔ ጓሮ መንደር እስኪለማ፤
"ደደቢት" እስክትሆን የእንዱስትሪ አውድማ፡
ጥሪቷ ተሟጦ ኢትዮጵያ እንድትደማ፡
አዜብ አረዳችን ቀዳማዊት ቀድማ፡፡
የሚያቀነቅኑት እኩይ ጠንቅ አላማ፡
ሚሾ ይሉት ተዝክር የዘመኑ ቅኝት የነጠላ ዜማ፡
የሚቀባበሉት ሹመኞች ፓርላማ፡
የሟቹን ራዕይ ማስቀጠል ጥምጠማ፤
ሃያ ዓመት ደልለው ለጎጥ ካቀኑማ፡
ባዶ ጉልት ከስረን ወረት ስንቀማ፤
ገለባ አስታቅፈውን ምርቱን ካሸሹማ፡
ለካስ ሲሸጡን ነው ከገዥ ሳንስማማ፡
የጸብ ቁርሾ ጭረው እኛ ስንዳማ፤
"ደደቢት" ‘ሲንጋፖር’ ኢትዮጵያ ቆዝማ፡፡
መሃል ሸገር ነግሰው ጣይቱ ከተማ፡
አገር ህዝብ አዳፍነው አውርሰው ጨለማ፡
የሚተያዩበት የጋን መብራት ሻማ፡
ዘር አጋ ለይቶ ጥሪት የሚቀማ፡
ያጎረሰ ነክሶ ትውልድ የሚያዳማ፡
ምንጭ የማያሻግር የጎጠኞች አድማ፡፡
መሰሪ ልባቸው እራሱ ታመማ፡
የቆረጡት ቅጥል በላቸው ያ! ሳማ፡
ሞታቸውን በሩቅ እኛ አንዳንታማ፡
አጎንብሰው ቀሩ ክፉ ሰው ጠማማ፡
መቸም ላይቃኑ እርቅ አይሹ ዶማ፡
በቅዠት አለፉ ቅንድባም ጠይባማ፡
በደም ሰክረው በዘር ባያሸልቡማ፡
ምን ይበጀን ኖሯል ከርመው ቢባጁማ፡፡
የጐንቻው ! yegonchaw@yahoo.co.uk
የጐንቻው !

No comments:

Post a Comment