Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Tuesday, April 23, 2013

በሲዳማ ህዝብ እያመጸ ነው


sidama
ሚያዚያ 6 ቀን 2005 ዓ ም ኢህአዴግ ብቻውን ሊያካሂደው የነበረውን ምርጫ አንቀበልም በማለት ከተለያዩ ወረዳ በትስስር የተቃወሙ የሲዳማ ብሔረሰብ አባላት መታሰራቸውን የጎልጉል ምንጮች አስታውቀዋል። ምንጮቹ እንዳሉት በአካባቢው ከፍተኛ ድጋፍ ያለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከምርጫው ራሱን ማግለሉ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዳገኘም አመልክተዋል።
በቀበሌ የመሰብሰቢያ አዳራሾች የታጎሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የብሔረሰቡ አባላት እንዲፈቱ በሚጠይቁና በታጣቂ ሃይሎች መላከል የተካረረ ግጭት ይነሳል የሚል ፍርሃቻ እንደነበር ያመለከቱት ምንጮች የሲዳማ ተወላጆች የታጠቁ ስለሆነ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ አንጋቾችን ማሰማራቱን አመልክተዋል።

ለምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው እጩዎቼ፣ ታዛቢዎቼና አባላቶቼ በእስር፣ በድብደባና ከሥራ በመባረር እየተንገላቱ ነው በማለት ራሱን ከምርጫው ያገለለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ፤ ከምርጫው በኋላም እስሩና እንግልቱ መቀጠሉን ማስታወቃቸውን፣ በአንድ ሳምንት 26 አባላቱ እስር እንደተፈረደባቸው፣ በሲዳማ ዞን በየወረዳው ጊዜያዊ ፍርድ ቤቶችና ሸንጎዎች እየተቋቋሙ የፓርቲው
እጩዎች፣ ታዛቢዎችና አባላት ከ400 ብር በላይ የገንዘብ ቅጣትና ከ3ወር እስከ አንድ ዓመት ከስድስት ወር የሚደርስ እስራት እየተፈረደባቸውና ፍርደኞቹ ወህኒ መውረዳቸውን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የደርጅቱ ጉዳይ ሃላፊ ዶ/ር አየለ አሊቶ በመጥቀስ ኢሳት ዘግቧል። የኢህአዴግ አመራሮች ከሳሽም ፈራጅም በሆኑበት ሁኔታ ዜጎቻችን እየተንገላቱ ነው፤ ከምርጫው ብንወጣም ትግላችን ይቀጥላል ማለታቸውን የኢሳት ዘገባ ያስረዳል። (ፎቶ: worancha blogpost)

source: goolgule.com
posted by Aseged Tamene

No comments:

Post a Comment