Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Thursday, April 25, 2013

"በሀገሪቱ የተደረገው ምርጫ የቧልትና የቀልድ ምርጫ መሆኑን ለህዝብ አሳውቀናል”

አቶ አስራት ጣሴ
አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ አስራት ጣሴ የዛሬ እንግዳችን ናቸው፡፡ አቶ አስራት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ዋና ጸሐፊና የመድረክ አመራር አባል ናቸው፡፡ የ33ቱ ፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴም ሰብሳቢ ናቸው፡፡ በወቅታዊ  የሀገሪቱ  ጉዳይ  ላይ  ከፍኖተ ነፃነት ጋር ቆይታ አድርገዋል  መልካም  ንባብ
ፍኖተ ነፃነት፡- የ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ እስካሁን ምን ምን አከናወኑ?
Asrat Tassieአቶ አስራት ጣሴ -የአንድነት ፓርትይ ዋና ፀሐፊ
አቶ አስራት፡- ከተፈራረምን 6 ወር የሆነን ሲሆን ተጨባጭ ሆኑ የስራ እንቅስቃሴዎችን አድርገናል፡፡ ከዚህም መካከል የሚያዚያ 2005 ዓ.ም. ምርጫን አስመልክቶ ለሀገሪቱ ይጠቅማሉ ያልናቸውን 18 ጥያቄዎችን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ለኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ፣ ለኢህአዴግ ጽህፈት ቤት በማቅረብ ምርጫውን ነፃ፣ፍትሃዊ፣ ተዓማኒና ሰላማዊ እንዲሆን ትልቅ ትግል አድርገናል፡፡ ነገር ግን ከእነሱ በኩል ምንም ዓይነት ምላሽ ባይገኝም በእኛ በኩል ውጤታማ ስራ ሰርተናል ብለን እናስባለን፡፡ በርግጥ ከ33ቱ ውስጥ 5ቱ ከተፈራረምን በኋላ ወደ ምርጫ ቢገቡም የቀሩት 28ቱ በሙሉ ይህ ምርጫ ፍትሃዊና ተዓማኒ ስለማይሆን አጃቢ መሆን አንፈልግም በሚል ከምርጫው ወጥተናል፡፡

ከምርጫው የወጣነውም ተገደን እንደሆነና ቢያንስ 18ቱም ጥያቄዎች ባይመለሱም እንኳ በመሰረታዊ ሐሳቦች ዙሪያ ውይይት ቢደረግበትና የተወሰኑ ጥያቄዎች እንኳ ቢመለሱና በትንሹ ምርጫው ከፈት ቢል ወደ ምርጫው እንገባ ነበር፡፡ በመሐል ፒቲሽን ፈርሞ ወደ ምርጫው የገባው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሲአን) ተመልሶ ወጥቷል፡፡ ስለዚህ በሀገሪቱ የተደረገው ምርጫ የቧልትና የቀልድ ምርጫ መሆኑን ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም አቀፉ ማኀበረሰብም አሳውቀናል፡፡ በዚህ ምርጫ መሳተፍ ለሰብዓዊ መብት መሻሻል፣ ለሀገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ዕድገት፣ የህግ የበላይነትና ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ ምንም ጥቅም እንደሌለው ነው የተረዳነው፡፡ በተፃፃራሪ መልኩ ያየነው እንደሆነ በዚህ ምርጫ መሳተፍ ማለት የሰብዓዊ መብት ጥሰትን፣ የዜጎች መፈናቀልን፣የዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰትን እንዲቀጥል መፍቀድና መቀበል ማለት ነው፡፡ ይህን ደግሞ የማንኛውም ሰው ህሊና የሚቀበለው ተግባር ስላልሆነ የጠቀስኳቸው የመብት ጥሰቶች በሀገሪቱ እንዲቀጥሉ ስለማንፈልግ ከምርጫው መውጣታችን ተገቢ ነው፡፡ ሌላው ትልቁ ውጤታማ ስራ የሆነው ሁሉም ፈራሚ ፓርቲዎች በየፓርቲያችን ከምርጫ ጉዳይ ባለፈ ወደፊት በጋራ ልንሰራቸው ስላሰብናቸው ስራዎች በሰፊው ተወያይተን የካቲት 23 ቀን 2005ዓ.ም በመኢአድ ጽህፈት ቤት በርካታ እንግዶች በተገኙበት የጋራ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመናል፡፡ፍኖተ ነፃነት፡- ወደ ፊት ሊያሰራችሁ የሚችል የመጨረሻ ሰነድ ነው ወይስ ከምርጫ ጉዳይ ውጭ ልትሰሩ አላሰባችሁም?

አቶ አስራት፡- የመጨረሻ የሚባል ሳይሆን በጋራ ለመስራትና ወጥ የሆነ አቋም ለመያዝ እንጂ  ከምርጫ ጉዳይ ባለፈ ወደፊት በተጠናከረ መልኩ በጋራ ሊያሰራ የሚችል ሰፊ ጥናት የተደረገበት ረቂቅ ተዘጋጅቶ ለየፓርቲዎቹ ተበትኗል፤ ፓርቲዎቹም ተነጋግረው ለሚቀጥለው ስብሰባ ይቀርባል፡፡ በበለጠ ለምረዳት እዚህ ላይ ይግለጡት

No comments:

Post a Comment