Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Monday, April 1, 2013

ለ አቶ አዲሱ ለገሰ የቀረበ የህልውና ጥያቄ ? ? ?

Addisu legeseለመሆኑ እርስዎ አማራ ነኝ ይላሉ ከዚያም አምራውን ወክለው ለ20 ዓመታት ፀረ-አማራ ፀረ- ኢትዮጵያ አገዛዝ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘው ይገኛሉ እናም የሕውሀት መሥራቾች እንደሚሉን ከቅድመ ደርግ በፊት የነበረውን የመላ የኢትዮጵያውያንን ተማሪዎች ንቅናቄ ፀረ ፊዳሊዝም ሣይሆን ለትግራይ ሕዝብ የበላይነት የነበረ ነው ይሉናል እርስዎም የታገሉለት ለዚሁ ነበር ?
እርስዎ የተወለዱት በሓረር ሁኖ ሳለ ግን እርስዎ ለምርጫ ለመወዳደር የምረጡት በበለሳ ወረዳ ዙይ-ዝሀየ አካባቢ ቆላ ሐሙሲት ነው ምክንያትዎ ግልጽ ነበር ?
ለምን ባማራው ክልል እንዲሆን ተደረገ ወይስ ባማራው ክልል ታማኝ ሎሌ የሚሆን ስለጠፋ ይሆን ?
ውድ የነፃ አውጭ አባት ነወትና ከርስዎ እውነት አይጠፋምና መልሱን በጉጉት እጠብቃለሁ:: 
 በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ምሥረት መርኀ ግብር ውስጥ አራት ነጥቦች በግልፅ ሠፍረዋል። ትግራይን ነፃ ለማውጣትና በሰላም የራሷ መንግሥት አቋቁማ እንድትኖር በቁጥር አራት የሠፈረው፤ በአማራው መቃብር ላይ የትግራይን የበላይነት እናቋቁማለን ይላል። ከዚህ መመሪያ ሌላው ነገር ሁሉ ይመነዘራል።
  • የአማራ መኖሪያ የሆኑትን የወገራ፣ የጠለምትና የዋግ ክፍሎች ወደ ትግራይ ከልሎ፤ የዚሁ ቦታ ነዋሪዎች የሆኑትን፤ ሀብታቸውን ዘርፎ እነሱን ከቦታቸው አፈናቅሎ አባሯቸዋል። የሱዳን ደንበሩንም እንዲሁ።
  • አማራው እስከዛሬ የበላይ ስለነበረ፤ ካሁን በኋላ ወደ ሥልጣን እንዳይመጣ በሩን ለአማራው መዝጋት አለብን ይላል። በተግባርም ፈፅሞታል።
  • አማራው ከየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ተጠራርጎ ወጥቶ በሠጠነው ክልል ብቻ ተዘግቶ ይኑር ይላል ተግባራቸው። ይህም ደግሞ፤ ንብረታቸውን በመንጠቅ፣ በእስር በማንገላታት፣ በመግደልና በማባረር ተግብሮታል።
  • የአማርኛ ተናጋሪ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ከሥራቸው አባሮ፤ ሌላም ቦታ ሠርተው እንዳይበሉ አድርጓቸዋል። በየመሥሪያ ቤቱ የነበሩትን አማራዎች በተመሳሳይ መንገድ ከሥራ አፈናቅሏቸዋል።
  • ደርግን አማራ እያለና የደርግን አረመኔነት የአማራ አረመኔነት አድርጎ፤ አማራን የትግራይ ወገናችን እንዲጠላው ማድረጉ፤ አማራውን የትግራይ ወገናችን እንዲያጠፋው ሆን ብሎ ማዘጋጀቱ ነው። በትግራይ ትምህርት ቤቶች፤ ይህ የደርግን አማራ ብሎ ማስቀመጡ፤ ትምህርት ተብሎ እየተሠጠ ነው።
  • የአማራ ድርጅት ብሎ ባቋቋመው፤ “ብሔራዊ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ” እንኳን፤ የሌላ ክፍል ወገኖቻችንን የሆኑትን አባላት በአመራር አስቀምጧል።
  • የአማራው ክልል ብሎ ባካለለው ቦታ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ንብረት የሆነው EFFORT ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ከመውሰዱም ሌላ፤ በክልሉ በሙሉ የበላይነት ያላቸው ትግሬዎቹ ናቸው።
  • በዚሁ ክልል ተብየው የተቀመጠው የአማራው ወገናችን፤ በማንነቱ እንዲያፍርና እንዲሸማቀቅ እየተደረገ፤ በያለበት በማንነቱ እየተሰደበና እየተዋረደ ይገኛል። ስድቡን እዚህ ማስፈሩ ማራባት ይሆናል።
  • በዚህ ሁሉ በሚደርስበት የዕለት ከዕለት በደል የተነሳ፤ ቦታውን ለቆ፣ ሀገሩን ጥሎ፣ ለበረሀ እንግልትና ለባህር አሣ ምግብ ሆኖ፤ ብልቶቹ እየተቸረቸሩበት፣ በውርደትና ሀፍረት እየተሸማቀቀ ለስደት የተዳረገው አብዛኛው የአማራው ወገናችን ነው 
    Source: http://www.facebook.com/semenawiw/posts/303324756415820

No comments:

Post a Comment