Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Friday, March 29, 2013

ኢትዮጵያውያን ደቡብ አፍሪካ የኢሕአዴግን ስብሰባ በተኑ፤ ቴዎድሮስ አድሃኖም ተደብቀው አመለጡ



ዘ-ሐበሻ) በደቡብ አፍሪካ ሮዝባንክ ከተማ የተጠራው የኢሕ አዴግ ሥብሰባ በኢትዮጵያውያን ብርቱ ትግል መቋረጡንና መበተኑን የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘገበ። በልማት ስም የተጠራውና በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የተጠራው ይኸው ስብሰባ የስር ዓቱ ደጋፊ የሆኑ ከ20 የማይበልጡ ሰዎች ቢገኙም ስብሰባው ይደረግበት የነበረውን ሃያት ሆቴል የስር ዓቱ ተቃዋሚዎች በመሙላት ስብሰባው እንዳይደረግ አድርገዋል።

የድምጻችን ይሰማ፣ የኦነግ፣ የግንቦት ሰባት እና የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላትና ደጋፊዎች በአንድነት የኢሕ አዴግን ስብሰባ እንዳይደረግ በማድረግ
- ከልማት በፊት የሕዝብ ነፃነት ይቅደም
- በቅድሚያ መገደብ ያለበት ወንዝ ሳይሆን የ ኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ነው በሚል ሕዝቡ ጩኸቱን በማሰማቱ ስብሰባው ተቋርጦ ደጋፊው ሕዝቡ ጥቃት ያደርስባቸዋል በሚል ፍራቻ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ደብቆ ከአዳራሹ አስመልጧል።

የኢሕአዴግ ስብሰባ እንዳይደረግ ያስተጓጎሉት ኢትዮጵያውያን ኢሕ አዴግ በከፈለበት የሃያት ሆቴል አድራሽ ስብሰባ በማድረግ በቀጣይ በአንድነት ስለሚያደርጉት የጋራ ትግል ዙሪያ መነጋገራቸውን፤ የተዘጋጀውን ውሃ እና መጠጥም የኛ ገንዘብ ነው በሚል እንደጠጡት የዘገበው የዘሐበሻ ሪፖርተር የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሃያት ሆቴል ስብሰባው ከተስተጓጎለበት በኋላ ደጋፊዎቹን በኢምባሲው ውስጥ መሰብሰቡ ታውቋል። ከኢትዮጵያ ኢምባሲ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ከሮዝባንክ ከተማም ኢትዮጵያውያን ወደ ኢምባሲው በመሄድ ተቃውሟቸውን እንዳሰሙም ሪፖርተራችን ጨምሮ ዘገቧል። zehabesha.com

No comments:

Post a Comment