Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Saturday, March 2, 2013

የሰላማዊ ትግል በብዙሃን መጋናኛ ጭምር ታግዞ በወያኔ መቀልበሱ እና መዘዙ



"ለዘመናት የህዝባችን ብሶት የወለደው ጀግናው ኢሕኣዲግ ሰራዊት ደርግ  ሲጠቀምበት የነበረውን የኣዲስ ኣበባ ራዲዮ ጣቢያን ለሰፈው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል። ጉንቦት ሃያ ሽህ  ዘጠኝ ሞቶ ሰማኒያ ሶስት ኣመተ ምህረት"።

እረወድያ "ፅድቁ ቀርቶብኝ በውጉ በኮነነኝ" ኣለ ያገ ሰው ያንዳንዱ ሽንገላ ልዋጥለት ሲል! እንዲህም ድርጎ የለ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ኢሕኣዴግ የኢትዮጲያን ብሄራዊ መገናኛ ኣገልግሎት ተቆጣጣረ። ይልቅ የኢትዮጲያን ቴላቪዝዮን እና ሬድዮን ወያኔ/ኢሕአዴግ ከሰው በላው ደርግ ነጠቆ ከዚያም የውሸት ውሽንፍር እና የሽብር ማዓት ሲረጭበት፤ ብሎም የኢትዮጲያን ህዝብ ሲያደናግርበት፤ የሰፊውን ህዝብ ልቦና ሲሰልብብበት ተስተውሉዋል በማለት ዛሬ ላይ ቆመን ፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። ይህም ወያኔ/ኢሕአዴግ እንደገቡልን ቃል ኪዳን ሳይሆን የኣብዮታዊ ደሞክራሲ ተልካሻ የፖለቲካ ትርፍ ለማገኘት የመገናኛ ብዙሃን እንደ ጠበል መርጫ እንዲሁም ኣልፎ ተርፎ ሲኖደሱን እና መጅሉስን እንደ ፖለቲካቸው ማጥመቂያ በማዋል ላይ ይገኛሉ። ይኽም ድርጊት የውያኔ/ኢሕአዴግ መሰሪ እና እኩይ  ተግባር ኣንዱ መሆኑን የሚያጋልጥ ነው።

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ ም  ኣሳይቶ ከነሳን ጊዜ ጀምሮ  ለሆዳቸው ያደሩ ጋዜጠኞችን ቀርቶ በኢትዮጲያ የህዝብ የመገናኛ ኣገልግሎት በሃገር መሪ ነኝ ባዮቹ በነመለስ ዜናዊ ጭምር የወያኔን ፖለቲካ የተቹ የተቀውሚ ድርጅት ኣባሎችን "መንገዳችሁን ጨርቅ ያድርግላቸሁ"፤ ለዘመናት ተከብሮ ለኣፍሪካ ጭምር የነጻነት መለያ  የሆነ ባንድራችንን "ጨርቅ እኮ ነው"፤ በመደጋገፍ ብረው የኖሩ ማህበረሰቦችን "ያይናችሁ ቀለም ኣላማረንም እና ከኢትዮጲያ ባስቸክዋይ ውጡ"፤ የሰለም እና እርቅ ጉባ በኢትዮጲያ ይጠራ ሲባሉ "ማን ተጣላ እና ነው" በማለት በሰላም ላይ ሲቀልዱ፤ የፖለቲካ ወይም የሃሳብ ተቃዋሚን በአሽሙር እስከ "ወራዳ" እያሉ በፓርላማ ውስጥ የተሰደቡበት፡ ታሪኩን እና ባህሉን የተወራረሰውን ኣንድ ህዝብ "ኣክሱም ለወላይታው ምኑ ነው"? መብቱን የጠየቀን ሁሉ "ሽብርተኛ እና ፀረ ሰላም" የመሳሰሉትን ጸያፍ ንግግሮች በመጠቀም እና ህዝብን በማሸማቀቅ ከመሪ የማይጠበቅ በዛኛው ዓለም ካሉት ፈልጭ ቆርጭ እንደ ጥሩ መልእክት በብቸንነት ወያኔ/ኢሕኣዴግ በሚጠቀምበት ሬድዮ እና ቴሌቪዝን ሰማንበት። 
 
ሃገርን ያለማንገራገር ያስገነጠለ እና በርካሽ የሸጠ ብሎም ህዝቦቹዋን በማዋረድ ገዳምን እና መስጊድን የደፈረ ከአማላክ ጋር በማወዳደር ሃይማኖተኛ ነኝ ባዩ ኣዲስ የተሾሙት ጠቅላይ ሚንስቴር ደግሞ ጉድ ሳይሰማ መስከርም ይጠባም እንደተባለው" ዘላለማዊ ክብር ለመለስ ዜናዊ" በማለት በዚህኛው ለም በህይወት ካሉት ተከታይ የሙት ራእይ ኣስፈጻሚ በብሄራዊ መግናኛ ገልግሎት ሲነገርበት ኣይተናልም ሰምታናልም። መለስ ዜናዊ ስኳር የተወደደው "ገበሬው ሻይ መጠጣት ስለጀመረ ነው" እንዳላሉን ሁሉ ተተኪው የህሌና ታሳሪም "ጤፍ የተወደደው የኢትዮጲያ ሃዝብ የኑሮ ሁኔታ ስለተተሻሻለ እና የጤፍ ተጠቃሚ በመጨምሩ ነው" ብለውናል። ይህ ነው እንግዲህ ዶሮን ሲጃጅሉዋት በመጫኛ ጣሉዋት ማለት ሰፊውን ህዝብ ያደኸየ ግን የኣንድ የፖልቲካ ፓርቲን ያገዘፈ እና ይን ያውጣ ውሸት ያውም በመግናኛ ኣገልግሎት በኩል እንደገና መደገም እጅግ የኢትዮጲያን ህዝብን መናቅ ነው። ምን ዋጋ ለው የታልቁን መሪ ራዓይ ብቻ  እንደሚተገብሩ እንጅ ምንም ለውጥ እና ማስተካከያ እንደማይኖር በዲፍረት በኢትይኦጲያ መግናኛ ኣግልግሎት ተገልጽዋል። To read the whole article please open the link

No comments:

Post a Comment