Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Saturday, March 9, 2013

ዋይታ ከጎግ አውራጃ ፤ ጋምቤላ፤

ከምዕራባዊው የኢትዮጵያ ክፍሎች ፣ ለዶቸ ቨለ ዋይታንም ሆነ ብሶትን የሚመለከቱ ጥቆማዎች ደርሰዋል ። አንዱ ፣ በጋምቤላ መስተዳድር ፣ በጎግ ወረዳ ደረሰ የተባለውን ግድያ ይመለከታል። በጎግ ዲፓክ ቀበሌ ፣ ጊሎ ወንዝ አቅራቢያ ፣ ወጣቶችና አርሶ
አደሮች ፣ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተገድለዋል የሚል ጥቆማ ከቀረበልን በኋላ ወደ አካባቢው ስልክ በመደወል ፤ አየን ፤ ሰማን ያሉ ሰዎችን፤ እንዲሁም የጋምቤላን መስተዳድር የፀጥታ ኀላፊ አነጋጋረናል ።
ከሰሞኑ ፤ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች መርኅ ግብር ፣ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ ከመጽደቁ በፊት ፣ በፍትኅ ሚንስቴር አዘጋጅነት ፤ ጠቃሚ የሆኑ ነጥቦችን ለማካተት፤  ይረዳል በሚል እሳቤ፣ የውጭ ሃገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፤ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የአፍሪቃ ቀንድ ተጠሪ በተገኙበት ፣ ባለፈው ረቡዕ ውይይት መደረጉን የሚያስረዳ  ዘገባ አሰምተን እንደነበረ የሚታወስ ነው።
ስለጉባዔው ከሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የቀረበውንም ትናንት አስደምጠናል። ሰብአዊ መብት ዐቢይ አጀንዳ ሆኖ በተመከረበት ወቅት ፤ እንዴት ከሰብአዊ መብት ይዞታ ጋር የተያያዘ  ዋይታም ሆነ ብሶት ተሰማ? በጎግ  ወረዳ ጋምቤላ ምንድን ነው የሆነው? ያነጋገርናቸው ያካባቢው ሰዎች እንዲህ  ብለውናል።-

ስለዚህ ዋይታም ሆነ ስሞታ መንግሥት ምን ይላል? የጋምቤላ መስተዳድር የፀጥታ ኃላፊ አቶ ጎርደን  ኮምግ--
ደቡብ ምዕራባዊው የኢትዮጵያ  ክፍል፣ ጋምቤላ፤ ባለፉት 9 ዓመታት ገደማ ፣ ከሰብአዊ መብትና የውጭ ባለወረቶች በዚያ ለግብርና ሰፊ ቦታ ስለማግኘታቸው ፣ የሠፈራ መርኀ-ግብርንም በተመለከተ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በተደጋጋሚ መወሳቱ አይታበልም።
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሰ ለማዳመጥ የኽንን ሊንክ ይክፈቱት http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_16659711_mediaId_16659701

No comments:

Post a Comment