Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Monday, December 17, 2012

ሥራችን ሲመዘን



ደግም ስንሰራ ክፉም ስንባዝን፡
የትኛው ነው ጥሩ እስኪ ለስማችን?

ደጎችም እኛ ነን ከፎቸም እኛ ነን፡
የቱ ያረካናል ስንገዛ ህሊናን?

አልምተንም አጥፊ ሁል ጊዜ ከሆን፡
ዞር ብለን ስናይ የትኛው ተሻለን?

አውጥተን ሰናወርድ ሁል ጊዜ ካለን፡
ፈልጎ ለማግኘት የትኛው ቀለለን?

ለዛሬ አሞግሰን ነገ ላይ ማዋረድ ከሆነ ልምዳቸን፡
ጓደኛ ለማገኘት ይህ ነው ወይ ዘዳችን?

ስንመክር ቆይተን ሴራ ከሸረብን፡
ተደብቀን አንቀር ወደትስ ደርሳለን?

ተካፍለን ሚስጥርን ስናማ መልሰን፡
የታል ሽልማቱ ደመወዝ ያገኝን?

ዛሬ ተወዳጅተን ነገ ላይ ከከዳን፡
ተጠቀምናልስ ወይ ውጤትስ አመጣን?

እውነተኛ መስለን እውሽት ከትናገርን፡
ሌላን አደናገርን ከቶ እንደት ተደሰትን?

ሳናድምጥ ሌላን ብቻ ስሙን ካለን፡
ጨመርን ወይ እውቀት በዓእምሮ ጎለበትን?

እዚህ ሁነን ሳለ እዛም ከተመኘን፡
በረከተልን ወይ ምን ጭብጥስ አገኘን?

እኛን መምሰል ትተን ሌላን ከተከተልን፡
የጃችንን ተተን እንላለን ወይ ኖረን?

ሰለዚህ እናስብ እስኪ ረጋ ብለን፡
ደጎችም እኛ ነን ከፎችም እኛ ነን፡
የቱ ያጋድላል ስራችን ሲመዘን?

ፅድቅ እና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም፡
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም፡
ብሎናል ዘፋኙ ያ ያለፈው ትውልድ፡
ህዝቡን አያዝናና ማስገንዘብ የሚወድ፡

በሉ ልብ እናድርግ ደግ ስራችን ያጋድል፡
በትዝብት ሚዛን ላይ እንዳንሆን ቀላል።

ተፃፈ ፡ በአርጋው 05ታህሳስ 2010

No comments:

Post a Comment