Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Saturday, December 8, 2012

በጂዳ የብአዴን ዝግጅት ላይ የተገኙ ተጠርጣሪ ኢትዮጵያዊያን ተባረሩ

Friday, December 7, 2012

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) 32ኛ አመት ለማክበር አርብ ምሽት በጅዳና በአካባቢዋ በተዘጋጀ ዝግጅት ለመሳተፍ የሄዱ በርካታ ነዋሪዎች እንዳይገቡ መከልከላቸውንና ስብሰባው በጊዜ መበተኑን ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ ከስፍራው ገልጿል።
ዛሬ በተጠራው የብአዴን ዝግጅት ላይ የተቃውሞ ድምጻችን እናሰማለን በሚል ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወረቀት በህቡዕ የበተኑ ሲሆን፤ በስብሰባው ላይ ተቃውሞ እንዳያካሂዱ በሚል ፍራቻ ጥሪ የተደረገላቸው አንዳንድ ግለሰቦች ከስብሰባው ውስጥ እየተጠሩ እንዲባረሩ መደረጉን ነዋሪዎች ለነቢዩ ሲራክ ገልጸውለታል። ለተጨማሪ መረጃ እዚህ ላይ ይጠቁሙ

No comments:

Post a Comment