Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Friday, February 1, 2013

የኢትዮጵያዊነት ልዩ ውበትና አንድነት እስከ ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ የመብት ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች የተንጸባረቁበት 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ

    Sports had the power “to change the world … to inspire … to unite people.”
Nelson Mandela
በፍቅር ለይኩን
Click here for PDF
Ethiopian footballer adane girma
የ1998ቱ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት የተካሄደው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ በዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ ስፖርት ለሰላም፣ ለወንድማማችነት፣ ለአንድነት… ወዘተ ያለው አዎንታዊ ፋይዳ በግልፅ የታየበት መድረክ ሆኖ ነበር ያለፈው፡፡ በአንድ ቡድን ተደልድለው የተገናኙት በጥንታዊ ስልጣኔዋኗ እስከ አስር ሺህ ዘመን በሚመዘዝ ግዙፍ ታሪኳ፣ ታላቅ የሆነ ብሔራዊ ኩራትና ስሜት ያላት ጥንታዊቷ ፋርስ የዛሬዋ ኢራን ብሔራዊ ቡድን፣ ከአሜሪካ አቻዋ ጋር በተፋጠጡበት መድረክ፣ የትናንትነዋ ኃያል ኢራንና የዘመናችን ልዕለ ኃያል አገር አሜሪካን ያገናኘ ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ነበር ያለፈው፡፡

በእነዚህ ሁለት ባላንጣ አገሮች በአንድ ቡድን ተደልድለው የተገናኙበትን ጨዋታ/ፉክክር የአሜሪካው እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በአጭር ቃል እንዲህ ሲሉ ነበር የገለጹት፡- “the mother of all games” በወቅቱም ስለ ሁለቱ አገራት ጨዋታ የዘገቡ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሁለቱ አገራት ፖለቲከኞች፣ ዲፕሎማቶች፣ የእግር ኳስ ባለሙያዎችና ተንታኞች ጨዋታው ከስፖርታዊ ውድድር ባለፈ ጠንከር ያለ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው ነበር ሲዘግቡ የነበሩት፡፡Please read the whole article by clicking here.

No comments:

Post a Comment