Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Wednesday, February 6, 2013

አገርን የመግደል፣ ትውልድን የማጥፋት ቀጣይ ሴራ

 
በሰደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ

Coordinating Committee of Exiled Members of Ethiopian Teachers’ Association
የተሰጠ መግለጫ

                                                                                                          ጥር 28, 2005ዓ.ም

አገርን የመግደል፣ ትውልድን የማጥፋት ቀጣይ ሴራ።

የወያኔ/ኢሕአዴግ ሥርዓት በአሁኑ ጊዜ በሁሉም የሥራ መስኮች ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰበት ያለው በምርጫ 2002 ዓ.ም የተጠቀመበትን የተደራጀ የልማት ሠራዊት መገንባት በሚለው አንድ ለአምስት ፖለቲካዊ አደረጃጀቱ ተማሪዉን አንድ ለአምስት እንዲደራጁ በማድረግ ( በእያንዳንዱ የመንግሥት መስሪያ ቤት በገጠርና በከተማ ተግባራዊ እያደረገ ያለው የስርዓቱ የአደረጃጀት ዘዴ ነው) በኢሕአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲ እንዲጠመቅ እርስ በርሱ እንዳይተማመን በጥርጣሬ ዐይን እንዲተያይ፣ በሃገር ጉዳይ ላይ በጋራ እንዳይመክር፣ በስርዓቱ ላይ ታቃውሞ እንዳያነሳ፣ የስርዓቱ አራማጅ ፣ ደጋፊና አገልጋይ ሆኖ እንዲቀጥል የዘረጋው የአፈና መዋቅር ትምህርት ቤቶችን አካዳማዊ እውቀት የሚገበይባቸው አምባዎች ሳይሆኑ የኢሕአዴግ የፖለቲካ አቀንቃኝ ተቋም እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

የወያኔ ሕገ መንግስት አንቀጽ 90 ንዑስ አንቀጽ 2 ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት ፣ ከፖለቲካ አመለካከቶችና ባሕላዊ ተፅዕኖዎች ነፃ በሆነ መንገድ መካሄድ አለበት ይላል። ሆኖም ግን ወያኔ ራሱ ያወጣውንና ቆሜለታለሁ የሚለውን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ በመጣስ የየትምህርት ቤቶቹ ር/መምህራን በየትምህርት ቤቶቹ የሚገኙ የኢሕአዴግ አባል የሆኑ መምህራንና ሠራተኞች ህዋስ ሰብሳቢ በመሆን በዋነኛነት የፖለቲካ ሥራ እንዲሠሩ ከመመደባቸውም በላይ ሲገመገሙም ዋነኛ መገምገሚያው የፖለቲካውን ሥራ ሰርተሃል ፤ አልሰራህም የሚል ነው። ም/ር/መምህራን ደግሞ በግልጽ በትምህርት ውጤታቸው በየክፍሉ ከ 1ኛ እስከ 10ኛ ብሎም እስከ 20ኛ ደረጃ የወጡ ተማሪዎችን በግዳጅ በወጣት ሊግ በማደራጀት የኢሕአዴግ አባልነት ወርሃዊ ክፍያ በማስከፈል፤ ሰላይ ተማሪዎችን በየክፍሉ ውስጥ በመመደብ የስለላ ሥራ እንዲሰሩ በማሰማራት ተግባር ተጠምደዋል።

የስለላ ሥራው የኢሕአዴግ አባል ባልሆኑ መምህራንና ሰራተኞች እንድሁም ተማሪዎች ላይ የሚካሄድ ቢሆንም በዋነኝነት ግን ተቃዋሚ ናቸው ተብለው በሚጠረጠሩ መምህራን ላይ የጠነከረ ከመሆኑም ባሻገር በየእለቱ በክፍል ውስጥ የሚናገሯቸው የትምህርት ይዘት ያላቸው ቃላት እንደ ጸጉር እየተሰነጠቁ በየትምህርት ቤቶቹ ለተቋቋሙት የወያኔ/ኢህአዴግ ህዋስ የሃይል መድረክ እስከ ከፍተኛው የኢህአዴግ የፖለቲካ አመራር ሪፖርት እየተደረገ በእያንዳንዱ መምህር ስም ባዘጋጁት የግል ማህደር መዝግበው በመያዝ የትምህርት፣ የሥራ፣ የሥልጠና ፣ የእድገት ፣ …. ወዘተ እድል ሲመጣ የእድሉ ተጠቃሚ እንዳይሆን ነጥሎ ለመምታት ይጠቀሙበታል። ለምሳሌ በሰኔ ወር 2004 ዓ.ም ለ2ኛ ድግሪ የትምህርት እድል (ድህረ-ምረቃ) 30 ፐርሰንት ( 30%) የሚይዘው ሙያዊ ስነ ምግባርን በሚመለከተው የመወዳደሪያ መስፈርት ስር ፤ የስራ ተነሳሽነት 6% ፣ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ 6% ፣ ለሙያዊ ስነ ምግባር ተገዥነት 6% ፣ ለሌሎች አርዓያ የሆነ 6% ፣ ለለውጥ ዝግጁ የሆነ 6% የሚል ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ሃረጎች በመጠቀም ያለምንም የመግቢያ ፈተና አባሎቻቸውንና ለዘብተኛ የሆኑ መምህራንን የትምህርት እድል ተጠቃሚዎች አድርገዋል። http://articles2u.files.wordpress.com/2013/02/eta-press-release-1956.pdf

No comments:

Post a Comment