Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Sunday, February 24, 2013

ወያኔ ታላቋን ትግራይ ለመመስረት በአማራ ላይ የሰራዉ በደል!!!

በ1991(እ.አ.አ) ወያኔ አዲስ አበባ በገባ ማግስት አንድ ደረቱን የነፋ የወያኔ ካዴሬ የአዲርቃይን ከተማ ህዝብ ሰብስቦ ‚እንደምታውቁት የትግራይ ግዛት ጠለምትንና አዲርቃይን አጠቃሎ የሰሜን ተራራዎችን ማለት ራስ ደጀንና ጃናሞራን ይጨምራል…‛ ብሎ ንግግሩን ሲከፍት በትዝብት ከሚሰሙት ህዝብ መካከል ፊታውራሪ ያይኔ የተባለ አዛውንት ተነስተው ‚ይህን ታሪክ ማነው የነገራቹህ? የነገራቹህ ሰው ፍጹም አሳስቷቹኋል። ትግራይ የሚባለው ግዛት ከተከዜ ወንዝ ማዶ ነው ከተከዜ ወዲህ ያለው መሬት ትግራይ ሆኖ አያውቅም። አሁንም ወደፊትም እንዳትሞክሩት ብለዉ መለሱለት። የሚያስደንቀው ነገር የሰቆጣ (ወሎ) ህዝብ ለወያኔ የሰጠው ምላሽ የአዲአርቃይ ህዝብ ከሰጠው ምላሽ ፍጹም ተመሳሳይ ነው። በ1991(እ.አ.አ) የሰቆጣን አካባቢ ወደ ትግራይ ለማዲረግ ወያኔ ሲከጅል የሰቆጣ ህዝብ የሰጠው መልስ ‚እኛ የዛጔዌ ዘር ነን ከማእከላችን ከላሊበላ ና ከመላዉ ከወሎ ህዝብ ወጥተን መኖር አንችልም።በታሪካችን የትግራይም ሆነን አናውቅም።‛ የሚል ነበር። በጊዜው የወያኔ መንግስት ያልተረጋጋ ስለነበር ከወሎ የወይራ ውሃን፣የአለማጣንና የኮረምን ለም አካባቢ ከጎንደር ደግሞ ከወልቃይት ጠገዴ በተጨማሪ ማይጸምሪ የተባለችውን ከተማ ማእከል በማዴረግ የዋልዲባ፣ የብራዋስያንና የጠለምት አካባቢብቻ በትግራይ ክልል አጠቃለለ ጠለምት የሚባለው በሰሜን ተከዜን ተከትሎ ተንቤንን፣ በምስራቅም ተክዜ ተከትሎ የዋግን አውራጃና በደቡብ የስሜን ተራራዎች የሚያዋስን ስትራተጂካዊ ደጋ፣ ወይና ደጋንና ቆላን የሚያካትት ቦታ ነው።
በአጠቃላይ ከጎንደር በጣም ለም መሬቶች ጠለምት፡ወልቃይት፡ጠገደና ሁመራ ወደ ትግራይ ተከልለዋል።
ከወሎ ኮረም፡አላማጣ፡ራያ አዘቦ፡አበርገሌ ጠቅለዉ ወደ ትግራይ ወስደዋቸዋል።

በ1991 (እ.አ.አ) በተደረገው ቅርጫ የቆቦ፣የአዲርቃይንና የስሜን ተራራን በይደር በአማራ ክልል እንዲቆይ ቢወሰንም በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ስለተደላደለ የአዲርቃይን፣ የስሜን ተራራዎችንና የቆቦን አካባቢዎች ወደ ትግራይ ክልል ለማጠቃለል እየቋመጠ ይገኛል።
          አረሱት ወልቃይትን ዘቅዝቀው እንደቦይ
          አረሱት አርማጮን ዘቅዝቀው እንደቦይ
          አረሱት ሑመራን ዘቅዝቀው እንደቦይ
          አረሱት ወፍላን ዘቅዝቀው እንደቦይ
          አረሱት ጨለምትን ዘቅዝቀው እንደቦይ
          አረሱት ጠገደን ዘቅዝቀው እንደቦይ
          አረሱት እንዳመሃሪን ዘቅዝቀው እንደቦይ
          አረሱት ራያ አዘቦን ዘቅዝቀው እንደቦይ
          አረሱት አበርገሌን ዘቅዝቀው እንደቦይ
          አባትየው ቢሞት ልጅየው የለም ወይ፤
          እረ ተላላ ነዉ፡ አገር ተላላ ነዉ፡ ይሄዳል እንደ ሰዉ፣
          ጀግና ጎበዝ ሄዶ፡ ወርዶ ካልመለሰዉ፤

Dictators like TPLF cancer (idiot) group search many reasons and ways instead of admitting their mistakes; prepare toys (forged Amaras) that can help them achieve their mission. These people coming to the district are illiterates sent to humiliate innocent people; for the last two decades they need the fertile land from Gondar and Wollo not the people that is why they made the district under their administration for NO history reference.

አንበሳ ነብር እኖሩበት መንደር፣
እነ ዶሮ መተዉ ያስካኩበት ጀመር፤
እረ ተላላ ነዉ፡ አገር ተላላ ነዉ፡ ይሄዳል እንደ ሰዉ፣
ጀግና ጎበዝ ሄዶ፡ ወርዶ ካልመለሰዉ፤
posted by Aseged Tamene at here

No comments:

Post a Comment