Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Thursday, February 7, 2013

ጄነራል ከማል ገልቹ “አልታሰርኩም” ይላሉ

What’s Ethiopian Review up to?

ኢትዮጵያን ሪቪው በመባል የሚታወቀው ድረ-ገጽ ኢዲተር አቶ ኤልያስ ክፍሌ ሰሞኑን አንድ ዜና ይዘው ነበር… “የኦሮሞ ነጻነት ግምባር (ኦነግ) መሪ ጀነራል ከማል ገልቹ ኤርትራ ውስጥ በእስር ላይ ናቸው” የሚል፣ ይሁንና ጄነራል ከማል ገልቹ “እኔ አልታሰርኩም ብለዋል”።

የኢትዮጵያን ሪቪው ድረ-ገጽ አዘጋጅ አቶ ኤልያስ ክፍሌ ቀደም ሲል መነሻውን ከኤርትራ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አመራር አባል ሆነው የነበረ ሲሆን ከግንባሩ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ግንባሩ አቶ ኤልያስንና አንድ ሌላ የቅርብ ጓደኛቸውን ከአባልነት ማስወገዱ ይታወቃል።
አቶ ኤልያስ ክፍሌ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አባል በነበሩበት ወቅት ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ረጂም ቃለ-ምልልስ አድርገው ነበር። ይህን ባለ አምስት ክፍል የቪድዮ ቃለ-ምልልስ በወቅቱ የተለያዩ ድረ-ገጾች ይዘውት ወጥተዋል።

በዛኑ ሰሞን አካባቢ አቶ ኤልያስ ክፍሌ እና ድረ-ገጻቸው ኢትዮጵያን ሪቪው የኤርትራውን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን “የአመቱ ታላቅ ሰው” ብለው መሾማቸውም ይታወሳል። ይህ እንኳ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያስደመመ ነበር።

አቶ ኤልያስ ክፍሌ ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አመራር አባልነት ከተወገዱ በሗላ መንደርደሪያቸውን ከወደ ኤርትራ ባደረጉ ግምባሮች ላይ የሚያወጧቸው ዜናዎች እና ዘገባዎች አንዳንዶቹ መሰረት የሌላቸው ሆነው ተገኝተዋል። ለምሳሌ በአንድ ወቅት አቶ ኤልያስ “የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር 21 አባላቱን ረሸነ” የሚል ዜና ይዘው ወጥተው ነበር። ግንባሩ ዜናውን ሀሰት ሲል ያጣጣለው ሲሆን ተገደሉ ከተባሉት አርበኞች መካከል አንዳንዶቹ በሕይወት መኖራቸውን በየሚድያው እየወጡ ተናግረዋል።

ሰሞኑን ደግሞ አቶ ኤልያስ “የኦነጉ መሪ ጄነራል ከማል ገልቹ ኤርትራ ውስጥ በእስር ላይ ናቸው” ብለው ነበር። ጄነራል ከማል ገልቹ ስለጉዳዩ ሲጠየቁ ፈገግ ብለው፣ “እኔም ዜናውን ሰምቻለው” ነበር ያሉት።
የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከጄነራል ከማል ገልቹ ጋር ያደረገውን ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ።
http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/5984

No comments:

Post a Comment