Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Thursday, January 10, 2013

ሙስሊም ሐበሾች የነጻነት ትግል ከግንቦት 20 እስከ ግንቦት 20

ግንቦት 20 ቀን 1870…

Click here for PDF
ግንቦት 20 ቀን 1870 በሙስሊም ሐበሾች ታሪክ ዉስጥ ልዩ ስፍራ ይዞ የሚገኝ እለት ነው:: አፄ ቴዎድሮስ ራሳቸውን መቅደላ አምባ ላይ በገደሉ በአራተኛ ዓመታቸው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆነው የነገሡት አፄ ዮሐንስ አራተኛ የአፄ ቴዎድሮስን ኃይማኖታዊ መሰረት ያለው ሀገራዊ አንድነት ግንባታ መርህ እጅግ በከፋ መልኩ የተገበሩ ንጉሥ ነበሩ:: የዚህ ፖሊሲያቸው ሰለባም የሰሜን ኢትዮጵያሙስሊሞች ነበሩ::
ግንቦት 20 ቀን 1870 በኢትዮጵያ ክርስቲያናት መካከል ለዘመናት ለዘለቀው (ቅባት፣ጸጋና ካራ ቡድኖችን ያስታውሷል) ቀኖናዊ ዉዝግብ እልባት ለመስጠትናሙስሊሞችን ለማጥመቅ ከደሴ ከተማ በስተሰሜን 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ቀለም ሜዳ (ቦሩ ሜዳ) በአፄ ዮሐንስ ዋና ወምበርነት አንድ ኃይማኖታዊ የክርክር መድረክ ተከፈተ:: ያ ለቀናት የዘለቀና የሸዋውን ንጉሥ ምኒሊክንና ሌሎች ስመጥር መኳንንትና ካህናትን ያሳተፈ ስብሰባ የተረቱ ክርስቲያን ሊቃውንትን እግር፣ እጅና ምላስን በማስቆረጥና የሐበሻሙስሊሞች ህልውናን አደጋ ላይ የሚጥል አስደንጋጭዉሳኔን በማሳለፍ ነበር የተጠናቀቀው::
የሰሜን ኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንዲጠመቁ ወይም ሀገር እንዲለቁ በይፋ ተነገራቸው:: ተጠመቅ ወይ አገር ልቀቅ የሚለው የአፄ ዮሐንስ አዋጅ ለኃይማኖታቸው ቀናዒ ለነበሩት የሰሜን ኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሚዋጥ አልነበረም:: እርግጥ ነው ከመሞት መሰንበት ያሉ ከእምነት ይልቅ ሹመትን የመረጡ የኢማም ሙሐመድ ዓሊ ወይም ራስ ሚካኤል(በኋላ ንጉሥ ሚካኤል)ዓይነት ግለሰቦችም ነበሩ:: እስኪያልፍ ያለፋል እንዲሉ አንዳንዶችም ለይስሙላ በመጠመቅ ቀን ቀን ክርስቲያን ማታ ማታ ሙስሊም መሆንን መርጠው ነበር:: ሌሎች ተሰደዱ:: እምነቴን ወይ ሞቴን ያሉ ደግሞ ጂሐድ አወጁ:: ይቀጥላል…
Ethiopian Muslims protest continue July 21, 2012x
                       ሽሆች ባገራቸው በውያኔ ተላላኪወች ሲበረበሩ!!

No comments:

Post a Comment