Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Tuesday, January 29, 2013

የወያኔን ሰላዮችን ከውጭ አለም ማጽዳት

ከእስከ ነጻነት

ኢትዮጵያ የነጻነት ቀንዲል ነች፡እንደ ስበሃት ነጋ ላሉ ባንዳ ወያኔዎች ግን ጣሊያንን አሸንፈን ለመላው የጥቁር ህዝብ የነጻነት ጎህ ቀዳጅ መሆናችን ኩራት ሳይሆን እፍረት ስለሚመስላቸው አገሪቷ ከነሰንደቅ አላማዋ ጥፍታ ማየት የዘወትር ጥረታቸው ነው፡ ሌት ተቅን የሚተጉትም ለዚህ ስለሆነ የኢትዮጵያዊነት ሰሜት ያላቸውን ሁሉ ማሰር፤ መግደል፤ ማጥፋት ዋና ትግባራቸው ነው፡ ይህም ተግባራቸው ከበረሃ እስከ አዲስ አበባ ከዛም ጎረቢት አገሮች ድረስ ዘልቆ አሁን ደግሞ ወደ ምእራብ ሐገራትም መጣሁ እያለ ነው።

ግን አገሪቷም ሆነ ባንዲራዋ ልትጠፋ አትችልም፡ ለጥቁር ህዝብ የነጻነት ጎህ የቀደደች መሆኗን ለማረጋገጥ በርካታ ሃገራት ከቅኝ ግዛት ነጻ ሲወጡ ባንዲራቸውን መሰረት ያደረጉት በኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ላይ ስለሆነ ባለም ዙሪያ ሲውለበለብ ይኖራል እንጂ ባንዳዎች እንደተመኙት ልትጠፋ አትችልም።

ባለፈው አበበ ገላው ላይ የተቃጣው የግድያ ሴራ ከወያኔ አድሎአዊ አገዛዝ፤ ሸሽተን በመጣነው ሁሉ ላይ የተቃጣ ዛቻ ነው በሚል አጠር ያለች ጽሑፍ በእንግሊዘኛ ቋንቋ አቅርቤ ነበር። በዛሬው ጽሁፌ ማተኮር የምፈልገው ወያኔ (ለኔ ወያኔ ማለት ለአላማም ይሁን ለጥቅም የዚህን አገዛዝ እድሜ የሚያራዝም ሁሉ ነው) እንዴት ተሰደን ባለንበት አገር ለማስፈራራት ብርታቱን አገኘ? እንዴትስ የወያኔ አባላት ሰላዮች እና እበላ ባዮች በውጭው አለም በዙ? እንዴትስ መመንጠር እንችላለን የሚሉትን ዝርዝር ጉዳዮች በተመለከተ ይሆናል። እባከውን በጠጨማሪ ላምንበ እዚህ ላይ ይጠቁሙት

No comments:

Post a Comment