Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Wednesday, January 30, 2013

ነፃ የወጣው የኦሮሞ ነፃ አውጪ

ዳኛቸው ቢያድግልኝ
Click here for PDF
ቀስ በቀስ ደረጃ በደረጃ የሰከነ የሃሳብ እድገት፣ ብስለትና መረዳት ከዘመናት ለውጥ ጋር መሻሻልን መፍጠሩ እውነት ነው። ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማኖር፣ ይልቁንም ደግሞ በነፃነት ለመኖር ከወራሪዎች ጋር በተደረገ ትግል ሁሉ ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ ተንቀሳቅሰዋል። ለዚህ ታሪክ ሥሪት የኦሮሞ ልጆች ያልከፈሉት መስዋዕትነት አልነበረም። ኢትዮጵያን ግብርና መራሽ ኢኮኖሚ እስከዛሬ ካቆያት ደግሞ ያለ ኦሮሞ ኢትዮጵያ የለችም። የዚያኑ ያህል ኢትዮጵያ ምሉዕ የምትሆነው ከየትኛውም ዘር ይፈጠር ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ክብር፣ እኩል መብትና ነፃነት ሲኖረው ነው።

በአንድ የዘመን ቅንፍ ውስጥ የተፈጠሩ የስህተት መንገድን እውነት ብለው የተቀበሉ የኩረጃ ትውልዶች ስለነጻነት ያነበቡትና ስለመገንጠል ተገነዘብን ያሉትን አምጥተው የሀገራቸውን አመሰራረትና ታሪክ ሳይሆን የአውሮፓ ታሪክን ባዩበት ዐይን እንደ ሰው ያስከበራቸውን ኢትዮጵያዊነት ኮንነዋል። አገር የፈጠሩ መስሎአቸው ኢትዮጵያን ለማፍረስም ከጠላት በላይ ተንቀሳቅሰዋል። በተለይ ኢትዮጵያን ምስቅልቅል ያደረጋትና ሁሌም ከሁዋላ ቀሮች አንደኛ የሚያደርጋት አበሳዋ የበዛው በዚሁ መሰረታዊ የእውቀት ረሃብም ጭምር ነው።

በዘሩ ትምክህት የነበረውም፣ ተጎዳሁና ተናቅሁ የሚለውም የመረጡት መንገድ ሥህተት ነበር። ያንን ስህተት እየደገሙ መሄድ ወይም አለባብሰው የሚበጀን ይህ ነው ከማለት ጥፋት እንዳይደገም አድርጎ ለመሄድ መነሳት እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ ነገር ነው። የኦሮሞ ነፃ አውጪ ድርጅትም ለኢትዮጵያውያን አበሳ መብዛት ይልቁንም ደግሞ የኦሮሞ ልጆት ልብ ውስጥ በሌሎች ላይ ጥላቻን በመትከል፣ ክፋትን በመስበክ ለረዥም ዘመናት የቆየ ድርጅት በመሆኑ በርካቶች የመከራቸው ምንጭ ሌላው ብሄረሰብ እንደሆነ አድርገው እንዲቀበሉ አድርጎ ነበር።
የበልጠ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጠቁ

No comments:

Post a Comment