Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Wednesday, January 23, 2013

የተከደነ ብቃት በዓለም አደባባይ ሲውል

“አንድ አዲስ ያልተጠበቀ ብርቅዬ ነገር”
ከዛሬ የከሰዓት በኋላ ኢሮ ስፖርት ትንተና የተወሰደ
ከሥርጉተ ሥላሴ 22.01.2013
South Africa Ethiopian fansመቼም ፍቅር ከነተፈጥሮው የሚገኝበት ሚስጢር ከእናትና ከማልያ ላይ ብቻ ነው። የማልያ ፍቅር ተጫዋቹን ብቻ ሳይሆን ታዳሚውንም በሙሉ ፈቃደኝነት የሚሰደምም … ዕጹብ ድንቅ ጥበብ ነው። የበቃ!

እግር ኳስ የዓለምን ህዝብ በፍቅር ክንፍ የሚያደርግ ጨዋታ ነው። ሌላው ቀርቶ የእግር ኳስ ህግጋትን በሚመለከትም ከዳኞች ባላነሰ ታደሚዊቹ በቂ ዕውቀት እንዳላቸው እገምታለሁ። ስለምን? በእግር ኳስ ጨዋታ ታዳሚው በባለቤትነት ስሜት መንፈሱንና አካሉን በፈቃዱ ለድንቡልቡሏ ውብ ተዋናይ በውዴታ ስለገበረ፤ ሰለለገሰ በቀላሉ ሜዳ ላይ ባለው ትዕይንት ብቻ መማር ስለሚቻል።
የተቀባው እግር ኳስ ዕልፍ አዕላፋትን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በፍቅር ብቻ ቤተኛ በሚያደርገው ስጦታው በሙያው የሰለጠኑ፤ በጸጋው የተካኑ የብርቅና ድንቅ ሰዎችም ማፍሪያ ተቋም ነው። እግር ኳስ በሰው ኃይል አሰላለፍና አደረጃጃትም ሆነ አመራር ከዓለም- ዓቀፍ ጀምሮ እስከታች ድረስ በተዋረድ ሰፊ ሰራተኞችን ያሰማረ የሥራ መስክ ነው።

እግር ኳስ በኢኮኖሚ አቅሙ ሆነ በዓለምዓቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ተጽዕኖ በማሰደር እረገድም አንቱ የተባለ ነው። ዘረኝነትን በመዋጋት እረገድም ግንባር ቀደም ሲሆን፤ በማህበራዊ ህይወትም ቢሆን ወሳኝ ድርሻ ያለው ዘርፍ ነው። እግር ኳስ የአንድ ሀገርን የባህል ደረጃ ከፍ ከሚያድርጉት ወሳኝ ክስተቶች አንዱ ሲሆን፤ አብሶ አዲሱን ትውልድ በፍቅር በመገንባት በኩልም የእራሱ መጠነ ሰፊ አስተዋፆ አለው። http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/5776

No comments:

Post a Comment