Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Thursday, January 17, 2013

አገር ማለት

በአያና ከበደ ከኖርዌይ
አገር በታሪክ በቋንቋ በሀይማኖት በልምድ በተስፋ በደስታና በመክራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው። አገር ማለት አያት ቅድም አያት የተወለዱበት አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየተከላከሉ ለሕዝብና ለመንግስት የሚጠቅም ሥራ ሠርትው እድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻችውን ተክተው የተቀበሩበት ጉድጓድ ነው። በመወለድ እትብት በመሞት አካል ከአፈሩ ጋራ ስለ ሚዋሓዱ የአገሩ አፈር ሕዝብ በላዩ የሚኖርበት ማለት ነው። እግዚአብሔር ከምድርዋ ፍሬ ሕይወት እንዲጋኝባት በማድረጉ አገር እያጠባች የምታሳድግ ፍቅርዋ በአጥንት በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ የሆነች እናት ማለት ነው። ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን በማየት ስለ ማደግ አባቶች በሕህወትና በሞት የሠሩበት ደግ ሥራ በአእምሮ ታትሞ ስለ ቀረ በአገር እስካሉ ሲታይ በስድት ሲሆኑ ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው። አገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሀብት በመሆኑ ድህነትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስከ ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድም አያትና ከአባቶች በጥብቅ የተሰጠ ያደራ ገንዘብ ነው ፡፡  http://assimba.org/Articles/Hager_Malet.pdf

No comments:

Post a Comment