Yakob's Point of Views and News, Ethiopian politics and News, Cultures, Musics etc

Thursday, January 17, 2013

ጥያቄዎቻችን በጆሮ ዳባ ልበስ ሊታለፉ አይገባም -ከ33ቱ የፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

                            የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ገዢው ፓርቲ ተገደው
                                እንዲሰሙ የማድረግ ህዝባዊ ትግል ይቀጥላል!!
ከ33ቱ የፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች ባቀረብነው ጥያቄ ዙሪያ በቀጣይ የጋራ አቋም ላይ የተሰጠ መግለጫ
  1. 1. መግቢያ
በአዳማ ከተማ በ2005 ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ ላይ ለማወያየት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰበሰበን ወቅት ከተሣታፊ 66 ፓርቲዎች 41ዱ ከጊዜ ሠሌዳው በፊት የውድድር ሜዳውን መስተካከል በሚመለከቱ አበይት የምርጫ ጉዳዮች ልንወያይ ይገባል ከሚለው ኃሣብ በመነሣት እና በጉዳዩ ለመግፋት ፔቲሽን ፈረምን፡፡ በመቀጠልም በ29/02/05 ዓ.ም 18 ጥያቄዎችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ /ኢብምቦ/፣ 13 ጥያቄዎችን ደግሞ በ08/04/05 ለክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት፣ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ጽ/ቤት አቅርበን ከቦርዱ ጥያቄአችሁ “ውሃ አያነሳም” በሚል ሙሉ በሙሉ ውድቅ መደረጉ በ10/04/05 ዓ.ም በቃል ሲገለጽልን፤ ከጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት፣ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ጽ/ቤት መልስ እየጠበቅን መሆኑን ገልጸን መልስ መጠባበቃችንን ቀጠልን፡፡
ነገር ግን ጥያቄዎቻችን ግልጽና የማያሻሙ ቢሆኑም ምርጫ ቦርድ “ጆሮ ዳባ ልበስ” በሚል ለጥያቄአችን መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ አፀደቅሁ ባለው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት በገዢ ፓርቲ አይዞህ ባይነት ወደ ምርጫው አፈፃፀም ገብቷል Please read more by Clicking here.

No comments:

Post a Comment